woreda-12

Spread the love

የሰንበት ዝግ መንገድ የህፃናት መጫወቻ ፕሮግራም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ታህሳስ 06/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የሰንበት ዝግ መንገድ የህፃናት መጫወቻ ፕሮግራም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ነፃነት እንዳሻው የቦታው በመገኘት የዕለቱን ፕሮግራም በማስመልከት እንደተናገሩት የቀዳማይ ልጅነትን ትኩረት በማድረግ በወረዳ ደረጃ ያሉ ህፃናት በተፈጠረላቸው ምቹ የመዝናኛ ስፍራዎች ላይ ወላጆች ልጆቻቸውን በማምጣት ህፃናት
በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ እንዲጫወቱና አምሯቸውን እንዲያድሱ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ያሉትሲሆን ትውልድን በተመጣጣኝና ለህፃናት ተገቢ በሆነ አካባቢ ላይ እየተዝናኑ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ማድረግና ማንነታቸውን መገንባትና ሀገርን መገንባት ነው በማለት ተናግሯል።
በመጨረሻም የፅ/ቤቱ ሀላፊዋ አክለውም በቀጣይ በየሳምንቱ ተጠናክረው የሚቀጥል መሆኑንየገለፁት ሲሆኑ በርካታ ህፃናት እንዲጫወቱና እንደ መልካም ጅማሮ ወስደን ተቋማችን ለሚከናውናቸው መጠነ ሰፊ ስራዎች የወረዳው ነዋሪዎችና የህፃናት ወላጆች ከጽ/ቤቱ ጋር
በተቆራኝቶ ለመስራት ቁርጠኛ በመሆን የልጆቻቸው ሙሉ ማንነት ላይ በጥልቀት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጨምረው አሳስበዋል።

የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ከዪኤንዲፕ /UNDP/ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለ132 ስራ ፈላጊ ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠሪያ ድጋፍ አደረገ
ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

ጽህፈት ቤቱ ከዪኤንዲፕ/UNDP/ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በክፍለ ከተማው ነዋሪና ስራ ፈላጊ ለሆኑ 132 ወገኖች የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣ የዶሮ መኖ፣ ኬጂና እንዲሁም የችብስ መጥበሻ ማሽን ድጋፍ አድርጓል። በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት፣ የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ኪዳነ ማሪያም የወረዳ
አመራሮችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት የታደሙ ሲሆን በUNDP ፕሮጀክት አስተባባሪነት ለወረዳው ስራ አጥ ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠሪያ የሚሆን ቁሳቁሰ ተበርክቷል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት እንደገለፁት በሀገራችን በሌላው አለም ከተለመደው ለየት ያለና ለዜጎቻችን ተጠቃሚነት የተረጋገጠ በርካታ ሰብአዊ ተግባራት ሲከናወኑ ከቆዩት መካከል አንዱ ነው ያሉ ሲሆን የዶሮ እርባታን በአግባቡና በጥንቃቄ በመጠቀም ዜጎች ከራሳቸውም አልፈው ለወገናቸው ምሳሌ መሆን አለባቸው ሲሉ አስገንዝበው በዘላቂ ውጤት ላይ በማተኮር ተወዳዳሪነት ያለው የአኗኗር ዘይቤን ማዳበር እንደሚገባም ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይአሳስበዋል።
ሌላኛው በመድረኩ የተገኙት የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ አቡኔ ሰዎች ሰርተው ከችግር ለመላቀቅ የሚያስችላቸውን ሁኔታ ለማመቻቸት የአየር ንብረት ለውጥ ፣ የአካባቢ የአፈርና የውሀ ጥበቃና ሌሎች መሰል ተግባራት ላይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ሰርተን ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ያሉ ሲሆን ዜጎቻችን ከጠባቂነት ልማድ ተላቀው የራሳቸው ገቢ እንዲኖራቸው ተቋማችን በርትቶ እየሰራበት ይገኛል
ለዚህም የማህበረሰቡና የስራ ፈላጊው ሚና የጎላ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የየካ ክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ኪዳነ ማሪያም በበኩላቸው በርካታ የስራ ዕድሎችን በማመቻቸት ከዚህ በፊት ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ስለመሆኑ አክለው ከድርጅቱ ጋር በመተባበርም ዛሬ ላይ
እየተደረገ ላለው አስተዋፅኦ ላቅ ያለ ምስጋና እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በመጨረሻም በዶሮ ቤት አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨባጫ በመስጠትና ለ122 ሰዎች የዶሮ መኖ ፣ ኬጅና ዶሮ እንዲሁም ለ10 ሰዎች ደግሞ የችብስ መጥበሻ ከነሙሉ አክሰሰሪው በአጠቃላይ በድምሩ ለ132 ዜጎች ማበርከት ተችሏል።

የወረዳ 12 ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት “ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገ ስብእናን ይገነባል”በሚል መሪ ቃል ለ 20ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የጸረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ የፓናል ዉይይት አካሄደ።

የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን 23/03/2017ዓ.ም

በየካ የወረዳ 12 ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት “ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገ ስብእናን ይገነባል” በሚል መሪ ቃል ለ 20ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የጸረ ሙስና ቀንን አስመልክ ከወረዳዉ ሴቶችና ወጣቶች ጋር የፓናል ዉይይት አካሄደ። በፓናል ዉይይቱ ላይም ሴቶችና ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ይህንን ቀን ስናከብር ሙስናን በመከላከል የሀገራች ንን እድገት በማስቀጠል ሴቶችና ወጣቶች ሀላፊነታቸዉን በመወጣት መሆን እንዳለበት ተገልጿል ።
በየካ የወረዳ 12 ዋና አፈ ጉባኤ ሲ/ር መሰረት ተስፋዬ እንደገለጹት የጸረ ሙስና ቀንን ስናስብ እንደ ሀገር በዋናነት ሙስናን በመከላከል ላይ ትኩረት በማድረግ ለመጪዉ ትዉልድ ለሴቶች ለወጣቶች ከሙስና የጸዳ ሀገርን በማስረከብ እንዲሁም በስነ ምግባር የታነጸ ትዉልድ መፍጠር እንደሚገባ
ገልጸዋል ።
በየካ የወረዳ 12 አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ማ/ጉ/ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ/ት ነጻነት እንዳሻዉ በበኩላቸዉ ሙስና የሀገር እድገትን የሚጎዳ መሆኑን ገልጸዉ ሙስናን መከላከል ላይ ሴቶችና ወጣቶች የጎላ አስተዋጽኦ እንዳላቸዉ ገልጸዋል። በየካ የወረዳ 12 ዋና ስራ አስ ጽ/ቤት የጸረ ሙስና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሙሉሰዉ ምስጌ በበኩላቸዉ የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን ከሙስና የጸዳች ሀገር እንድትኖረን የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ሴቶችና ታዳጊ ወጣቶች ላይ በሰፊዉ በመስራት ሙስናን በመከላከል በየደረጃዉ ሀላፊነታችንን በመወጣት መሆን እንዳለበት አብራርተዋል። አቶ ሙሉሰዉ አክለዉም ሙስናን በመከላከል እንደ ሀገር የጀመርነዉን እድገት ማስቀጠል በስነ ምግባር የታነጸና ሙስናን የሚጸየፍ ትዉልድ መፍጠር ላይ ሴቶች እንዲሁም ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ። በመጨረሻም በቀረበዉ ሰነድ ላይ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ
በመስጠት የፓናል ዉይይቱ ተጠናቋል።

የየካ ወረዳ 12 አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ስልጠና ሰጠ ።
ህዳር 19/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

የየካ ወረዳ 12 አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ስልጠና ሰጥቷል ። በዕለቱ ስልጠናውን የሰጠው ጽ/ቤቱ የወረዳው ሰራተኞች አቅማቸዉን እንዲያሳድጉ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በያዘው እቅድ መሰረት የስልጠና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ሲሆን በዚህ ስልጠና ላይም ለቡድን መሪዎችና ለጽ/ቤት ፎካል ፐርሰን የስልጠናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ።
በዋናነትም በሁለት የስልጠና ርእሶች ላይ ትኩረት በማድረግ ማለትም በመንግስት ሰራተኞች መተዳደሪያ አዋጅ 56/2010 ላይና በአዲሱ ስታንዳርድ ዙሪያ ላይ ከክፍለ ከተማ በተመደቡ አሰልጣኞች አማካኝነት ስልጠናው ተሰጥቷል ::

በወረዳው ለስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ ፈጠራ እና የማይንድ እሴት ስልጠና ተሰጠ

ህዳር 19/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር የስራና ክህሎት ፅ/ቤት በየካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የስልጠና አዳራሽ ለወረዳው ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ ፈጠራና የማይንድሴት ስልጠና ሰጥቷል። የወረዳው ም/ል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልጀዋድ ኸይሩ በስልጠናው ላይ ተገኝተው ስለ ስልጠናው ወጣቶች እንዴት ያላቸውን ፀጋ መለየት እንዳለባቸው እና በለዩት ፀጋ ያላንዳች መሰላቸት ና በከፍተኛ ጥረትና ትጋት ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ገልፀው ወጣቱ ትውልድ ውጤት ያለድካም ጥረት እንደማይገኝ አውቆ በመስራት ህይወቱን ማሻሻል አለበት
ብለዋል። የአይኪው ኮሌጅ ባለቤትና የቢዝነስና የስብና ግንባታ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ እሱባለው ደባሽ የአመቱ ውጤታማ ጉዞ፣ራስን መገምገም፣ስራ ፈጠራ፣ሁለንተናዊ የህይወት ዘርፎች እንዲሁም የግልና የቤተሰብን ህይወት ማሻሻል በሚሉ ፅንሰ ሀሳቦች ዙሪያ ለወጣቱ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል። ወጣቱ እስካሁን ከሄደበት የሂይወት ኪሳራ ወጥቶ ወደሚያተርፍበት የህይወት መንገድ ለመሄድ ፀጋውንና ጥበቡን ለይቶ በዛ መንገድ መመላለስ ሲችል ነው ያሉት አሰልጣኙ ወጣቱ አዕምሮውን እና ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም የህይወት ግቡን ማሳካት ይችላል ብለዋል።

በወረዳ ደረጃ ለ30 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መራዘሙ ተገለፀ ።

ህዳር 02/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

ቀደም ሲል በወረዳ ደረጃ ለሰላሳ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት በድጋሜ መራዘሙ ተገልጿል ።የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የየካ ወረዳ 12 አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ትግስት መልስ እንደገለፁት ቀደም ሲል ሲሰጥ የነበረው የምዝገባ ሂደቱ ከተቋሙም ባለፈ የህዝብ ፍሰት ባለባቸው የወረዳ አስተዳደሩ ቀጠናና ብሎኮች
እንዲሁም አደባባዮች ላይ በስፋት ተደራሽ ማድረግ ስለመቻሉ ጠቁመው የፋይዳ ምዝገባው በመራዘሙም በድጋሜ አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል ። በተያያዘም ወ/ሮ ትግስት ለአገልግሎቱ የሚመጡ ተገልጋዮች ከዚህ በፊት እንደተለመደው የሚያስፈልጉመስፈርቶችን በመያዝ ማለትም ፓስፖርት ፣ መንጃ ፈቃድ ፣ የማንኛውም ባንከ ቡክ ፣ የወረዳ መታወቂያ እንዲሁም እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ደግሞ የልደት ሰርተፊኬት ይዘው በየካ ወረዳ 12 አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የእድሉ ተጠቃሚ
ይሆኑ ዘንድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የካ ወረዳ 12 አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የጥንቃቄ መልዕክት
አስተላለፈ፡፡
የካወረዳ 12ኮሙኒኬሽ ጽ/ቤት መስከረም 16/2017ዓ.ም

የካ ወረዳ 12 አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ዳባ የወረዳ አስተዳደሩና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስራ አመራር ኢንስቲቱዩሽን በጋራ እንኳን ለ2017 የመስቀል ደመራ በዓል አደረሳችሁ እያሉ የወረዳው ነዋሪ በዓሉን በማስመልከት ሰፊ የኤሌክትሪክ ፍጆታና ሰፊ መዝናናት ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉ ድንገተኛ አደጋ እራሱን ብሎም ቤተሰቡን እንዲከላከሉ እያስገነዘቡ የሚከተለውን የጥንቃቄ መልዕክት
አስተላልፈዋል፡፡ ደመራ በሚጀመርበት ስፍራ ተቀጣጣይ ከሆኑ የነዳጅ ማደያዎች ፣የኤሌክትሪክ እና የስልክ ምሰሶዎች አካባቢ እንዳይሆን ከፍተኛጥንቃቄ ያድርጉ፣ችቦና በእርጥበት ምክንያት አልቀጣጠልም ቢሉ ፈሳሽ በሆኑ ጋዞች ከማቀጣጠል ይቆጠቡ ፣ ችቦ በሚለኮስበት ወቅት እቤት ውስጥ ምንጣፎች እንደዚሁም ሌሎች ቁሶች ላይ በማረፍ እንዳይቀጣጠሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደዘሁም ርችት በመለኮስ በነዳጅ ማደያዎችና በሌሎች ተቀጣጣይ ቦታዎች ላይ አርፎ አደጋ ስለሚፈጥር ርችት መጠቀም ፈጽሞ የተከተከለ እንደሆነ በመልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም ኃላፊው የበኩሎን ጥረት እያደረጉ ካቅም በላይ ለሚገጥሞህ ችግር የወረዳው አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስራ አመራር ኢንስቲቱዩሽን እርሶን ለማገልገል 24 ሰዓት የሚሰራ መሆኑን እየገለጸ አንቡላንስና ሎሎች ችግሮች በሚያጋጥማችሁ ወቅት በ939 ነጻ መስመር ላይ በመደወል ማሳወቅ ትችላላችሁ እያሉ በዓሉ የሰላም ፣የደስታ እንዚሁም የአንድነት በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ የመልካም
ምኞት መልዕክታቸውን ገልጸዋል፡፡

የየካ ወረዳ 12 አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ላይ 11,300 ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ ።

ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

የየካ ወረዳ 12 አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ላይ 11,300 ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልጿል ። በሩብ አመት አፈፃፀም ያስመዘገባቸው አጠቃላይ ተግባራትን በማስመልከት የወረዳው ኮሙኒኬሽን በወረዳው ንግድ ጽ/ቤት በመገኘት መጠይቅ ያደረገ ሲሆን በዚህ መሰረትም ከበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ተግባራት መካከል በገቢ አሰባሰብ ላይ 11,300 ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ተብሏል ።
በየካ የወረዳ 12 አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ኩሳ ባይሳ በወረዳ ደረጃ አጠቃላይ ከንግድ ስርአቱ ጋር በተያያዘና በክትትልና ቁጥጥሩ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀማቸው ምን ይመስላል ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ እንዲህ ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተውናል ፦
በክትትልና ቁጥጥሩ ላይ የታደሰ እና ያልታደሰ በሚል በር ለበር በመለየት ደረጃ በሩብ አመት 497 ታቅዶ በድግግሞሽ ለ3668 ነጋዴዎች ተደራሽ ተደርጓል ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለ24 ሰአት ፣ ለ5 ቀንና ለ30 ቀን በሚሉት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያዎች አማካኝነት እርምጃ ወስደናል ብለዋል ።
71 በሚሆኑ የንግድ ተቋማትና ድርጅቶች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ በማድረግና ወደ ህጋዊ የንግድ ስርአት እንዲመጡ ከማድረግ በተጨማሪ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ፋይሎችን ኦዲት ማድረግ ተችሏል ያሉት አቶ ኩሳ 190 የሚሆኑ የኦዲት ግኝት አድርገን ከነዚህ መካካልም በ22ቱ ላይ ዘላቂነት ያለው የማጥራት ስራ ለመስራት ለሚመለከተው አካል ግኝታችንን በግልባጭ ልከናል ሲሉም አብራርተዋል ።
አያይዘንም በግንዛቤ ፈጠራው ዘርፍ የተሰራ ስራ በሚል ጠይቀን በአዋጅ ቁጥር 980/2008 ላይ በወጣውና በተሻሻለው 1150/2011 ደንብቁጥር እንዲሁም 461/2012 ደንብ ቁጥር መሠረት ለ450 ነጋዴዎች ለመስጠት ታቅዶ መድረኮችን በመፍጠር ለ473 ነገዴዎች ግንዛቤ ተደራሽከማድረግ በተጨማሪ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለስራ በሚወጡ ጊዜ ነጋዴዎች አላስፈላጊ ቅጣት ውስጥ እንዳይገቡ በማድረግ የግንዘቤ ማስጨበጫው ተግባር በስፋት ሲከናወን የቆየ ስለመሆኑ ተብራርቷል ። በመጨረሻም ከባለድርሻ አካላት ጋር የነበረ የስራ ላይ ቁርኝትን በሚመለከት አያይዘን ጠይቀን ከአቅም በላይ የሆኑ የህግ ጥሰቶች ሲያጋጥሙ ከወረዳ አስተዳደሩ ደንብ ጽ/ቤት ፣ ከፖሊሶችና ከአመራር አካላት ጋር በመጣመር ህጋዊ ሽፋን በማግኘት
ህገ ወጥ ነጋዴዎች ሲያጋጥሙ ህግና ስርአቱ በሚያዘው መሰረት ተዳኝተው ህጋዊ የንግድ ስርአትን እንዲከተሉ የማድረግ ሰፊ ስራ በመስራት ወረዳ አስተዳደራችን ሰላማዊና ጤናማ የሆኑ የንግድ ማህበረሰቦችን ይዞ በመራመድ ላይ ይገኛል ሲሉየማጠቃለያ ምላሽ የሰጡን የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪው አቶ ኩሳ ባይሳ ናቸው ። እንደ ወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትም ህግና ስርአትን ባማከለ መልኩ የህግ የበላይነትን መሠረት ያደረገ የንግድ ስርአት ለማስፈን በተለይም ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ እስከ ገቢ አሰባሰብ ድረስ የተከናወኑ የሩብ አመቱ አመርቂ ተግባራትን
በመመልከቱ በቀጣይ ባሉት ቀሪ የሩብ አመት ተግባራት ላይም የተገኙ ጥንካሬዎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲል
ገንቢ አስተያየቱን አካፍሏል ።

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር የስራ ክህሎት ፅ/ቤት በ1ኛ ሩብ አመት ለ264 ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉ ገለፀ ።

ጥቅምት 01/02/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

በዛሬው ዕለት በካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር የስራ ክህሎት ፅ/ቤት የ1ኛ ሩብ አመት ተግባራት አፈፃፀምን በማስመልከት በተቋሙ ተገኝተን መጠይቅ ያደረግን ሲሆን በዚሁ አማካኝነትም ለ264 ዜጎች በተለያዩ የስራ አመራጮች ላይ የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉ ተገልጿል በ2017 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት ላይ የወረዳው የስራ ክህሎት ጽ/ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ምናሉ ታደሰ “ሰፋ ያለ ቅድመ ግንዛቤ በመፍጠር ስራ አጥ ዜጎች የራሳቸው ገቢ እንዲኖራቸው በማድረግ በሩብ አመት አፈፃፀማችን ለ264 ስራ አጥ ዜጎች በተለያዩ የስራ አመራጮች የስራ ዕድል በመፍጠርና ተጠቃሚ በማድረግ የሩብ አመቱን አፈፃፀም የተሻለ ማድረግ ችለናል” ብለዋል ።

አቶ ምናሉ አክለውም በሩብ አመቱ ይህ ብቻ ሳይሆን አስተዳደሩ በአጠቃላይ በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ሁሉ በትስስር መልኩ እየሰራን የቆየንበት አግባብ ነበረ ያሉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የማዕድ ማጋራት ላይ ብቁ ተሳትፎ በማድረግና ከዚህ ባለፈም ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ዜጎቻችን የህይወት ዋስትና እንዲያገኙ በሚያስችላቸው መልኩ በተከታታይ የቅድመ ግንዛቤ ማስጨባጫ ተግባራትን አከናውነናል ሲሉ አብራርተዋል ።
አያይዘንም አሻራ ለመሙላት የሚመጡ ተገልጋዮች ከጽ/ቤታችሁ በር ላይ ለሚስተዋለው የሰው ሀይል ክምችት የተወሰደ መፍትሔ አለ ወይ ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ ቀደም ሲል የሚፈጠር የነበረ መሆኑና ችግሩን ለመቅረፍ በቀን መመዝገብ የሚገባንን የሰው ሀይል ብዛት በመወሰን በወረፋ አድርገን
ከምንመዘግበው ውጭ በር ላይ ማንም ሰው ያለአግባብ እንዳይቆም በማድረግ ችግሩን በቀላሉ መቅረፍ ችለናል ብለዋል አቶ ምናሉ ።
የወረዳ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በበኩሉ በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ላይ በስራ ዕድል ፈጠራው ዘርፍ በዚህ መልኩ የጀመረውን አመርቂ አፈፃፀም በልዩ ትኩረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ብርቱ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ምዝገባ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እየሆነ ስለመሆኑ ተገለፀ ።

ጥቅምት 05/2017 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ምዝገባ ለማህበረሰቡ የሚሰጠው ጠቀሜታና ተደራሽነት እንዲሁም አጠቃላይ ሂደቱን በማስመልከት በዛሬው ዕለት የወረዳው ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት በየካ ወረዳ 12 አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በመገኘት ቅኝት አድርጓል ።
የየካ የወረዳ 12 አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት መልስ እንደገለፁት የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ አገልግሎቱ ለማህበረሰቡ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን ስለ አጠቃላይ ሂደቱ አስመልክተን ባደረግነው ሁሉን አቀፍ ጥያቄ መሰረትም ምዝገባው ከናሽናል አይዲ ፣ ከቴሌና ከሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጋር በጋራ እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም አብዛኛው ተመዝጋቢ ጠቀሜታውን ቀድሞ በመረዳት በተቋማችን እየመጣ አገልግሎቱን እያገኘ ነው ያሉት ወ/ሮ ትግስት በየቀጠናው በተመደቡ አመራሮችና አደረጃጀቶች አማካኝነት ለ1 ወር የሚቆይ አገልግሎት ከመሆኑ ጋር በተገናኘ መረጃው የሌላቸውና ጠቀሜታውን አቅልለው የሚረዱት ካሉ በሚል የግንዛቤ ፈጠራ በመስራት ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል ። አገልግሎቱ ሲሰጥ ራሱን የቻለ ባለሙያ ተመድቦለት እየተከናወነ ከመሆኑም በላይ ከደንብና ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራና በተቀላጠፈ መልኩ በመስጠት ደህንነቱ የተረጋገጠና የተጠበቀ ዲጅታል አቀፍ
አገልግሎት ስለመሆኑም ጨምረው አብራርተዋል ወ/ሮ ትግስት ። የወረዳው ኮሙኒኬሽን በበኩሉ ተቋሙ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚበረታቱ መሆናቸውን በመግለፅ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ምዝገባን አስመልክቶ እየተሰጠ ያለውን ፈጣንና ጥራቱን የጠበቀ
አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ብርቱ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

2016 የ ስ ድስ ት ወራት የ ፅ /ቤቶች የ ስ ራ አ ፈፃ ፀ ም የ ተሻ ለ  እ ን ደ ነ በ ር  ተገ ለ ፀ

መጋ ቢት 11/07/2016 ዓ.ም  የ ካ ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

አ ገ ል ግሎት አ ሰ ጣጡን  አ ማስ መል ከ ት ምል ከታ ተካሄ ደ ።

 13/072016 ዓ.ም የ ካ  ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽን Read More

ደማቅ ባህላዊ እሴቶቻችን ለህብረ_ ብሔራዊ አንድነታችን

የ የ ካ  ክፍለ  ከተማ ኮ ሙኒ ኬሽን  ፅ ህ ፈት ቤት ያ ስ ጀመረ ው የ አ ን ድ ሳ ምን ት የ ማህ በ ራዊ ሚዲያ  ገ ፅ  ማሳ ደግ የ ን ቅና ቄ መር ሀ  ግብር  በ ወረ ዳ 12 ቀጥሏል

መጋ ቢት 16/07/2016 ዓ.ም የ ካ ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

የ መን ግስ ት ሰ ራተኞች የ ችግኝ  ተከላ  ን ቅና ቄ ተካሄ ደ

መጋ ቢት 17/07/2016 ዓ.ም የ ካ ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

ስ ፖር ት ከ ጤን ነ ትም ባ ሻ ገ ር  ለ ትምህ ር ት ያ ለ ው ሚና  ወሳ ኝ  መሆኑ  ተገ ለ ፀ  ።

19/07/2016 ዓ.ም የ ካ  ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

የ የ ካ  ክፍለ  ከተማ ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  የ ህ ብረ ተሰ ብ ተሳ ትፎና  በ ጎ  ፍቃድ ማስ ተባ በ ሪ ያ  ፅ /ቤት በ ር ካታ የ በ ጎ  ፍቃድ ስ ራዎች የ ተከና ወኑ  መሆና ቸውን  ገ ለ ፀ

መጋ ቢት 20/07/2016 ዓ.ም የ ካ ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

“አ ዲስ  አ በ ባ ን  ለ ህ ፃ ና ት የ ተመቸች ከተማ ለ ማድረ ግ የ ጀመር ነ ውን  ስ ራችን ን  አ ጠና ክረ ን  እ ን ቀጥላ ለ ን !!

አ ቶ ያ ደሳ  አ ብር ሃ ም

በ የ ካ  የ ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  ዋና  ስ ራ አ ስ ፈፃ ሚ

መጋ ቢት 27/2016 የ ካ  ወረ ዳ 12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

ጽ/ቤቱ የ ወረ ዳው ሰ ላ ምና  ፀ ጥታ ቀጣይነ ት ለ ማረ ጋ ገ ጥ ከ ነ ዋሪ ዎች ጋ ር  የ ሰ ላ ም ኮ ን ፈረ ን ስ  አ ካሂ ደዋል

መጋ ቢት 23/2016 ዓ.ም የ ካ  ወረ ዴ12 ኮሙኒ ኬሽንRead More

በ የ ካ ክፍለ  ከተማ ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  እ የ ተሰ ራ ባ ለ ው  የ መን ገ ድ አ ካፋይ ፕሮጀክት ላ ይ የ ችግኝ  ተከላ ን ቅና ቄ ተጠና ክሮ ቀጥለ ዋልRead More

በ የ ካ  ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  የ ውስ ጥ ለ ውስ ጥ መን ገ ዶች ጥገ ና  ስ ራዎች እ የ ተከና ወኑ  መሆና ቸው ተገ ለ ፀRead More

በ የ ካ  የ ወረ ዳ 12 ባ ህ ል  ኪነ ጥበ ብ ቱሪ ዝም ጽ/ቤት በ 9 ወራት ዉስ ጥ በ ር ካታ ተግባ ራት እ ን ዳከና ወነ ተገ ለ ጸ ።Read More

ለ ሁለ ተኛ ምዕ ራፍ የ ሴፍቲኔ ት ተጠቃሚዎች የ ግን ዛ ቤ ማስ ጨበ ጫ ስ ል ጠና  ተሰ ጠRead More

በ የ ካ  ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  የ ኦ ሮምያ  ል ማት ማህ በ ር  አ መታዊ ኮን ፈረ ን ስ  ተካሄ ደRead More

የ የ ካ ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  የ አ ር ሶ  አ ደር ና  ከተማ ግብር ና  ል ማት ፅ /ቤት የ ከተማ ግብር ና  ስ ራዎች ላ ይ ውጤታማ ተግባ ራትን  ያ ከና ወነ  መሆኑ ን  ገ ለ ፀRead More

የ ወረ ዳ 12 አ ስ ተዳደር  የ ሲቪል  ምዝገ ባ ና  የ ነ ዋሪ ነ ት አ ገ ል ግሎት ፅ /ቤት አ ገ ል ግሎቱን  ለ ነ ዋሪ ዎች ተደራሽ ማድረ ጉን  ገ ለ ፀRead More

“ሰ ላ ማችን  የ ህ ል ውና ችን  ቁልፍ፤  የ ብል ፅ ግና ችን  መሰ ረ ት ነ ው!” በ የ ካ  የ ወረ ዳ 12 ሠላ ም ሠራዊት አ ባ ላ ት።Read More

መስከረም 8/2016 ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሚኒኬሽንRead More

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር  አጠቃላይ የሴቶች ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ ::

መስከረም 11/2015ዓ.ም የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን

በየካ ወሰዳ 12 አስተዳደር የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ህብረተሰቡ በሠላም ወጥቶ በአደባባይ የሚያከብራቸውና የአብሮነታችን ማሳያዎቻችን በመሆናቸው ሴቶች የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ከጸጉረ ልውጦች ራሱን በመከላከል ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የድርሻቸውን ማበርከት እንዳለባቸው የወረዳዉ የሴቶች እና ህጻናት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ወይንሼት ዘሪሁን በዛሬው እለት በተካሄደው የሴቶች መድረክ ላይ ገልፀዋል።

በተያያዘም የወረዳዉ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ እድል ፈጠራ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት የወዳነሽ ተክሌ እነዚህ የአደባባይ በዓላቶቻች የኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚፈጥር ከሀገራችን አልፎ የዓለም ቅርስ በመሆናቸው አጠቃላይ ሴቶች የሰላም ባለቤት በመሆን ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በሚያጠነክር መልኩ መከበር እንዳለባቸው ተነገረ።

የውይይቱ ተሳታፊ ሴቶች  በበኩላቸው በዓላቶቹ የሃገራችን ትልቅ ሃብት በመሆናቸው ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበሩ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።[/read]