
አቶ ጫሊ ቤኛ
የየካ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪሰና የሰዉ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ
መግቢያ
በክ/ከተማ አስተዳደሩ እየተካሄደ የሚገኘውን የለውጥ ሂደት ተከትሎ በየዘርፉ በርካታ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ ሲሆን እነዚህን ማሻሻያዎች በዘላቂነት ለማስቀጠል እና መሰረት ለመጣልቀጠይነት በለዉ መንገድ የሚተገበር ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። የመንግስት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ሲባል “የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ” በፌደራል መንግስት ደረጃ ፀድቆ ወደ ተግባር ለማስገባት እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ይህንን ፖሊሲ ወደ ተግባር ለመቀየርና ብሎም ክ/ከተማ አስተዳዳሩ ላይ የሚታየውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለማስተካከል ችግር ፈቺ የሆነ እቀድ አቅዶ መተግባር አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አራት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች /አምዶች/ በተደረገው ጥልቅ ውይይት መለየት ተችሏል።እነዚህም ተወዳዳሪና ውጤታማ የሰው ሀብት ስራ አመራር መፍጠር፣ አገልግሎቶችን በማዘመን ተደራሽና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፣ ብቁና ስትራቴጂክ ተኮር ተቋም መገንባት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የህብረተሰብን ተሳትፎ ማሳደግ ቁልፍ የሆኑ የትኩረት መስኮች ናቸው፡፡ ይህንን ተግባራዊነቱን ማረጋገጥ የሚቻለው በሁሉም የአስተዳደር ዕርከን የሚገኘው የመንግስት አስፈፃሚ አካል በዕቅዱ ላይ ሲሳተፍ፣ ሲመራ፤ ሲከታተል፣ ሲገመግምና የመፍትሔ አካል መሆን ሲችል ነው፡፡ በመሆኑም ለቀጣይ የሚመራበት ሰነድ ሆኖ ያለፉትን የአፈጻጸም መነሻ በማድረግና የመጪውን የከተማውን ፍላጎትና ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ተልዕኮና መድረሻ ግብ ግምት ውስጥ ማስገባት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
- የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮ ፣እሴቶች፣ ሀላፊነትና ተግባር የጽ/ቤቱ ራዕይ
የአገልጋይነት ባህሪ የተላበሰ፣ ብቁ፣ ነፃና ገለልተኛ ፐብሊክ ሰርቪስ በመገንባት ዘመናዊና ውጤታማ አገልግሎት በማቅረብ በ2022 ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት የሆነ ተቋም ተፈጥሮ ማየት፣
- የጽ/ቤቱ ተልዕኮ
አገልግሎትን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በመዘርጋት ብቃትን መሰረት ያደረገ የሰው ሀብት ልማት፤ ስምሪትና አስተዳደር አገልግሎቶችን በመስጠት እንዲሁም ስትራቴጂክ ተኮር ተቋማትን በመገንባት የክትትል፣ ድጋፍና የቁጥጥር አገልግሎቶችን በመስጠት የአገልግሎት ውጤታማነትን በማሻሻል የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ነው፡፡
- የጽ/ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት
- የተቋም አቅም ግንባታ ሥራን የሚያሳልጡ ዘመናዊ አሰራሮችንና ተሞክሮዎችን በመለየት በክ/ከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ አስፈላጊዉን የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀብት ልማት በቀጣይነት የሚለማበትንና ጥቅም ላይ የሚዉልበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤
- የተቋማት አደረጃጀት ጥናት ላይ አስፈላጊዉን ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤ አግባብነቱን ይመረምራል፣ ያጸድቃል፤
- የክ/ከተማው አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባራት ጥናት ያካሂዳል፤ ውጤቱን ለካቢኔ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተገቢዉን ይፈጽማል፤
- በክ/ከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተገቢዉ ስታንዳርድ መኖሩን ያረጋግጣል፤ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤ ያጸድቃል፤ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤
- በክ/ከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻፀም ይከታተላል፣ የተገልጋዩን እርካታ ጥናት ያካሂዳል፣ የጥናቱን ውጤት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
- የመንግስት ሰራተኞች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለዉ መንገድ መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን እንዲሁም ዉጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
- ያልተማከለ የአስተዳደር ስርዓትን ለማጠናከር የሚያስችል የማስፈጸም አቅም ግንባታ ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- የመንግስት ሰራተኞችን ወቅታዊ አፈፃፀም ምዘና የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፤
- የመንግስት ሰራተኛ በብቃትና በአፈጻፀም ላይ የተመሰረተ የምደባ፣ የደረጃ ዕድገትና የእርከን ጭማሪ፣ የጥቅማጥቅምና የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፤ ዉጤታማነቱን ይገመግማል፣ አስፈላጊዉን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፤
- አግባብ ያለው የፌደራል ሕግ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመንግስት ሰራተኛው የሚያስፈልጉ የሥራ መደቦች፣ የትምህርት የስልጠናና የሥራ ልምድ አጠቃላይ መመዘኛዎች ያወጣል፤
- የመንግስት ሰራተኞች አቀጣጠር፣ አመዳደብ፣ የደረጃ እድገት፣ ዝዉዉር፣ አበልና ጥቅማ ጥቅም፣ ስልጠናና የዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያ ያወጣል፤ በህግ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
- በህግ መሰረት የክ/ከተማ አስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ለማቆየት በሚቀርብ ጥያቄ ላይ ዉሳኔ ይሰጣል፤
- የክ/ከተማ አስተዳደሩን የሰዉ ሀብት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ያደራጃል፤
- የህዝብ አገልጋይነት አስተሳሰብ ያለዉ አመራርና ፈጻሚ ይገነባል እንዲገነባ ይሰራል፣ የብቃት ማረጋገጫ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤ ያረጋግጣል፤
- በሚዘረጋቸው አዳዲስ አሰራሮች፤ አደረጃጀቶችና ማኑዋሎች ዙሪያ አጫጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- ሁሉም ተቋማት ዉጤታማ አፈጻፀም እንዲኖራቸዉ የሚያደርጋቸዉን አዳዲስ የለውጥ መሳሪያዎች ከራሳቸዉ ባህርይ አንጻር አጥንተው እንዲያቀርቡ ያበረታታል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፡፡
1.3.4 የጽ/ቤቱ እሴቶችና መርሆዎች
- የሰው ኃይላችን ሀብታችን:-
- አገልጋይነት:-
- ብቃትና ሜሪት:-
- ነፃና ገለልተኛ:-
- ፈጠራና ልህቀት :-
- ቅልጥፍናና ውጤታማነት
- ብዙሃነትና አካታችነት:-
የየካ ክፍለ ከተማ እስታንዳር































































[/Read ]