Peace and Security Office

Spread the love

አቶ ሀብታሙ ደረጀ ነጋሳ

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምናየጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

መግቢያ
የክፍለ ከተማው ኃላፊ መልዕክት

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የክፍለ ከተማውን የሰላምና የጸጥታ አስተዳደር ጉዳዮች የማስተዳደር እና ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ሃላፊነቶች ተቀብሎ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ምልዓተ ህዝቡን በማሳተፍ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች ከሌሎች ህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በክፍለ ከተማችን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያትና አጋጣሚዎችን በመጠቀም ለመፈጸም ታቅደው የነበሩ የስርዓት አልበኝነት፤ የወንጀል፤ የሁከትና ብጥብጥ እና የሽብር ተግባራት እንዳይሳኩ ከማድረግ በተጨማሪ የሚከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ክብረ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ በማድረግ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የክፍለ ከተማችን የሰላም የጸጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች በተቋም አቅም መፈጸም የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየተደረጉ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ ሆነው የክፍለ ከተማችን ሰላምና ጸጥታ ለማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጣቸው በየደረጃው የሚገኙ በሰው ሃይል ፤በግብዓት፤ በአሰራር እና በአደረጃጀት በማጠናከር ተልዕኮውን በተገቢው የሚፈጽም የህግ አስከባሪ ተቋም እንዲሆኑ ማድረግ ጊዜው የሚጠይቀው ሃላፊነት እንደ መሆኑ መጠን የክፍለ ከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ መላው የክፍለ ከተማችን ህዝብ እና ተቋማት በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማሳተፍ ከሚቻልባቸው ዘዴዎች መካከል ድህረ-ገጽ አንዱ እንደ መሆን መጠን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ድህረ-ገጽ በመጠቀም ሰላም፤ ጸጥታ እና ህግ ማስከበርን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በመሆን የዜግነት ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ::አመሰግናለሁ! አቶ ሀብታሙ ደረጄ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
በሰላም መጣችሁ።

ራዕይ
በ2022 አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት፤

ተልዕኮ
የተቀናጀ የጸጥታ ጉዳዮች አስተዳደር እና የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወንጀልን በመከላከል፤ የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በሃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል መከባበርና መቻቻል እንዲሰፍን በማድረግ፤የክትትል፤ ቁጥጥር እና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት፣ ነዋሪውንና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ባለቤትነት በማረጋገጥ ሰላም፣ ጸጥታናደህንነቷ የተጠበቀ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው

እሴቶች
ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት
ሚስጥር ጠባቂነት
ፍትሐዊነትና ሰብዓዊነት
ታማኝነትና ተጠያቂነት
ተቋማዊ አጋርነት
የህግ የበላይነትን ማክበርና ማስከበር
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ስልጣንና ተግባር

  • የደንብ ማስከበር ባለሥልጣንን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
  • የብሔራዊ የፀጥታና የሰላም ፖሊሲን መሠረት በማድረግ የከተማውን የአስተዳደርና ፀጥታ
    ጉዳይ ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ከተማ አቀፍ ፖሊሲ ይቀርፃል፤ ስትራቴጂ ይነድፋል፤ ህግ
    ያመነጫል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
  • በፀጥታ ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር ዋና የፀጥታ አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤
  • ለፀጥታና ሰላም አስጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ተገቢ የሆነ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፤ አስፈላጊ
    ሆኖ ሲገኝም እንደ አግባብነቱ ራሱ ወይም ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት የእርምት
    እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
  • የግጭት መንስዔዎችን በጥናት ይለያል፣ ግጭት እንዳይከሰት ይከላከላል፤ ሲከሰትም ባህላዊና
    ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ይፈታል፤
  • በከተማው ልዩ ልዩ ሀይማኖትና ቤተ-እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን
    ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብነት ካላቸዉ የፌደራልም ሆነ የከተማው
    አስተዳደር አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር
    ይሠራል፤
  • በግጭት መከላከል፣ አያያዝም ሆነ አፈታት፣ በነዋሪው ደህንነት፣ ሰላም እና ፀጥታ አጠባበቅ
    ጉዳዮች ዙሪያ አግባብነት ካላቸው የፌደራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር እና ሌሎች አካላት
    ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ያደርጋል፤ እንደአግባብነቱ ችግሮችን በተናጠል ወይም በጋራ
    ይፈታል፤
  • ህግና ስርዓት መከበሩንና የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት መጠበቁን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
  • ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና በስውር የነዋሪውንና የመንግስትን ጥቅም ጉዳት
    ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ድርጅቶችን በመከታተል ነዋሪውንና
    ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤
  • ከጸጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታ እና አቤቱታዎችን ይቀበላል፤ ይመረምራል፤
    እንዳግባብነቱ ራሱ ወይም በተጠሪ ተቋም ወይም በሌሎች በሚመለከታቸው አካላት
    ቅሬታዎቹና አቤቱታዎቹ መልስ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • በፌደራል መንግስት የተመዘገቡ እና ፈቃድና እድሳት የተሰጣቸውን የሀይማኖት ተቋማት
    እና የብዙሀን ማህበራት ለመረጃነት ይመዘግባል፤ መረጃ ያደራጃል፤ ህገ-መንግስቱንና ሌሎች
    ህጎችን አክብረው ስለመስራታቸው ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ እንዲወሰድ
    ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፤
  • ለህግ አስከባሪ አካላት እና ለነዋሪዎች በወቅታዊ ጉዳዩች ዙሪያ አቅማቸውን በመገንባት
    የህዝብ አገልጋይነት ሚናቸውን እንዲወጡ ያደርጋል፤
  • የሌሎች ህጎች ድንጋጌዎችና አሰራሮች እንደተጠበቁ ሆነው የጦር መሳሪያ ፈቃድ በሚመለከት
    የትብብር ደብዳቤ ይሰጣል፤ መረጃ ያደራጃል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት
    ይሰራል፤
  • በከተማው የጦር መሣሪያ አጠቃቀምና አያያዝ በተመለከተ የምዝገባ አፈጻጸምን ይከታተላል፤
  • የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ወንጀል፣
    የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ የማስተባበር ስራዎችን
    ይሰራል፤ ተፈጽሞ ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት በህብረተሰብ ተሳትፎ ላይ እና በመስፈርቱ መሰረት
    ስለመከናወኑ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
  • የፀጥታ ሁኔታ መረጃ ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፣ ውጤቱን
    ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
    አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
  • የመንግስትና የግል ተቋማትን እና ነዋሪውን በአካባቢያቸው የፀጥታ፣ ሰላም እና ተያያዥ
    ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉበትን ስልት ይቀይሳል፤ ተቋማዊ አደረጃጀት ይፈጥራል፤
    ያስተባብራል፤
  • በከተማው ክልል ውስጥ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ከሌሎች
    ባለደርሻ አካላት ጋር በመተባበር የጉዳቱ መጠን እንዳይባባስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፤
    በአደጋው ክልል ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰብ አካላት የህይወትና የንብረት ደህንነት እንዲጠበቅ
    ያደርጋል፤
  • ስለሰላማዊ ሰልፍ፣ በአደባባይ ላይ ስለሚከናወኑ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ስብሰባዎች
    ከንቲባውን ያማክራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም የአካባቢ ቅጥር ጥበቃ በተመለከተ ከሚመለከታቸው
    አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
    ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችና ውጤታቸው
    ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስክ
    ስትራቴጂያዊ ውጤት
    የጸጥታ መረጃ
    ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ
    የጸጥታ ኦፕሬሽን
    የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ
    የሰላም ግንባታ
    የዳበረ እሴትና አብሮነት የሰፈነባት ከተማ
    የህብረተሰብ ተሳትፎ
    የህዝብ የሰላም ባለቤትነት
    • የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ የስራ ሂደቱ የሚሰጥ ተግባራት
      የስራ ሂደቱ ባለድርሻ አካላት
  • የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
  • የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ
  • የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
  • የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
  • የፕላንና ልማት ኮሚሽን
  • ፍትህ ፅ/ቤት
  • የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
    ዋና ዋና ተግባራት የደንበኞች ፍላጎት
    1.ወንጀልን መከላከል፣ የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ-ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
    2 .ወንጀልን መከላከል፣ የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ-ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለፀጥታ ደህንነት አስጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰድ የፀጥታና ደህንነት ስጋቶች ላይ ፍትሃዊና ወቅታዊ ወቅታዊ እርምጃ እንዲወሰድ ግጭትን መከላከል፣ ማስተዳደር እና መፍታት ግጭት እንዳይፈጠር መከላከል፣ ከተፈጠረ ማተዳደር እና መፍታት
  • 3.የማህበረተሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክትትልና ቁጥጥር የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሲ አገልግሎት አፈጻጸም ላይ ወቅቱን የጠበቀ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲካሄድ
  • 4. የመንግስትና የግል ተቋማት ደህንነት ክትትልና ቁጥጥር የተቋማት የቅጥር ጥበቃ ላይ ወቅቱን የጠበቀ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር የቅንጅት ስራዎችን ማከናወን ከባድርሻ አካላት ጋር ወቅታዊ እና ችግር ፈች የሆነ ቅንጅትስራ እንዲኖር
  • 5.የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲያጋጥም የህይወትና የንብረት ደህንነት እንዲጠበቅ ማድረግ፤የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚያስከትሉትን የደህንነት ስጋት እንዲወገድ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሰላም ሚኒስቴር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ህዝባዊ አደረጃጀቶች የሚዲያ ተቋማትየፀጥታና መረጃ ዘርፍ የስራ ሂደቱ ተግባራት የስራ ሂደቱ ባለድርሻ አካላት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የ ፖሊስ መምሪያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
  • ፍትህ ፅ/ቤት የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤ የሰላም ሚኒስቴር የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት ጉምሩክ ኮሚሽን
  • የደንበኞች ፍላጎት
  • 1.ጥናትና ምርምር ማድረግ
  • በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ችግር ፈቺና ወቅቱን
  • የጠበቀ ጥናትና ምርምርእንዲካሄድ
  • 2.የፀጥታ መረጃ አገልግሎት
  • ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ የፀጥታ መረጃ አስተዳደር
  • ተግባራዊ እንዲደረግ በማስፈለጉ
  • 3.የፀጥታ ስጋቶች መለየት የፀጥታ ስጋቶች በወቅቱ እንዲለዩና እንዲቀንሱ
  • 4.ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት ወቅታዊ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ
  • 5.የጦር መሣሪያ አጠቃቀምና አያያዝ ምዝገባ አፈጻጸም ክትትል የጦር መሳሪያ ምዝገባ፣ አያያዝና አጠቃቀም ወቅቱንና
  • ህጉን ጠብቆ ስለመከናወኑ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ
  • 6.ሰላማዊ ሰልፍ፣ የአደባባይ ላይ ኩነቶችና ስብሰባዎች አፈጻጸም መከታተል ሰላማዊ ሰልፍ፣ የአደባባይ ላይ ኩነቶችና ስብሰባዎች
  • በወቅቱ ደንነታቸው እንዲጠበቅ ከጸጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታ እና አቤቱታዎች መቀበልና ምላሽ መስጠት
  • ከጸጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታና አቤቱታ በወቅቱ እንዲፈታ የአዲስ አበባ ንግድ ፅ/ቤት ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
  • የሚዲያ ተቋማት የሃይማኖት እና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስራ ሂደቱ ተግባራት የስራ ሂደቱ ባለድርሻ አካላት
  • ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት፤
  • ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት
  • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት፤
  • የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት
  • ዋና ዋና ተግባራት
  • የደንበኞች ፍላጎት
  • 1.የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ወቅቱን የጠበቀ እና ተገቢነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሰጥ ወቅታዊ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ ችግር ፈቺና ወቅቱን የጠበቀ የዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ የሰላም ዕሴት መገንባት ባህላዊ እና ወቅታ የሰላም እሴት ግንባታ እንዲካሄድ የሃይማኖት ተቋማት መረጃ መመዝገብና ማደራጀት የሀይማኖት ተቋማት ወቅቱን እና ጥራቱን ጠብቆ እንዲመዘገቡና መረጃቸው እንዲደራጅ ለሃይማኖት ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ ወቅቱን የጠበቀ ችግር ፈች ድጋፍ ለሃይማኖት
  • ተቋማት እንዲደረግ
  • የትምህርት ተቋማት
  • መምሪያ
  • ትምህርት ፅ/ቤት
  • የሰላም ሚኒስቴር
  • የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የስራ ሂደቱ ተግባራት
  • ዋና ዋና ተግባራት
  • የደንበኞች ፍላጎት
  • 1 የህብረተሰብ ተሳትፎ ማጎልበት ወቅቱን የጠበቀ የህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲገጎለብት የማህበረሰብ አቀፍ ፀጥታ አጠባበቅ ተግባራዊ ማድረግ
  • በራስ ተነሳሽነት የአካባቢ ፀጥታ ማስከበር ፍላጎት የሰላምና ጸጥታ አደረጃጀቶችን ማደራጀትና ማጠናከር የሰላምና ጸጥታ አደረጃጀቶች በወቅቱ ጥራቱን ጠብቆ እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ የብዙሀን ማህበራት በመረጃነት መመዝገብ፣ ማደራጀት እና ድጋፍ ማድረግ የብዙሃን ማህበራት ወቅቱን እና ጥራቱን ጠብቆ መረጃቸው የተመዘገበና የተደራጀ እንዲሁም ተገቢ ድጋፍ እንዲደረግ የስራ ሂደቱ ባለድርሻ አካላት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የሰላም ሚኒስቴር የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፤ የትምህርት ተቋማት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፌዴራል ሲቪክ ማህበራትና ድርጅቶች ኤጄንሲ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ህዝብ አደረጃጀቶች ደንብ ማስከበር ባለስልጣን