News(ዜና የካ)

Spread the love

የየካን ከፍታ እናረጋግጥ አሻራችን እናኑር” በሚል መሪ ሀሳብ በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በመንግስት ካፒታል ተሰርተው የተጠናቀቁ እና በመሰራት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ጉበኙ

ጥር 18/2017ዓ.ም

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታን ጨምሮ የክፍለ ከተማና እና የወረዳ አመራሮች በክፍለ ከተማው ስር ባሉ ወረዳዎች በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት ካፒታል የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የትምህርት ቤት ማስፋፊያና ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታ፣ የህፃናት መዋያ (ዴይኬር)፣ የእንጀራ ፋብሪካና የጤና ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የ2ኛው ዙር የኮሪደር አካል የሆነውን የየቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማትን ተዘዋውረው ጉብኝተዋል።

በጉብኝቱም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ እንደገለፁት “የየካን ከፍታ እናረጋግጥ አሻራችን እናኑር” ብለን በጀመርነው መሰረት ቅድሚያ ለትምህርት፣ ለህፃናት እና የጤና ዘርፍን በማስቀደም ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን የተማሪ ጥምርታውን በማስተካከል ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ለመስጠት የሚያስችል ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል።

በህብረተሰቡ ተሳትፎና በመንግስት ካፒታል እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ 7/24 እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ብርሃኑ ረታ አክለዋል። የትምህርት ቤት ተጨማሪ G+4 የመማሪያ ክፍል ግንባታዎቹን በ55 ቀናት አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ 7/24 እየተሰራ መሆኑን በጉብኝቱ ላይ ተገልፆል።

ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተከናወነ ያለውን ርብርብ እና የስራ ፍጥነትን ጎብኝዎቹ ያደነቁ ሲሆን ስራውን ለማጠናቀቅ 7/24 በመስራት የስራ ባህልን ከመቀየር ባለፍ የበርካታ ዜጎችን ህይዎት የቀየረ መሆኑንም አብራርተዋል። የወረዳ 01 የህፃናት ማቆያ ዴይኬር፣ የቅዱስ ማርቆስ ትምህርት ቤት፣ ህዝባዊ ሰራዊት ትምህርት ቤት፣ የወረዳ 02 ፖሊስ ጣቢያ፣ የንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ቤት፣ አድዋ በር ቅድመ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የወረዳ 11 የህፃናት መዋያ ዴይኬር፣ የካ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ ህንፃ፣ የወረዳ 12 ሸማች ህብረት ስራ ማህበር የእንጀራ ፋብሪካ፣ የካራሎ ትምህርት ቤት ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታ እና የወረዳ 09 የህፃናት መዋያ ዴይኬር የጉብኝቱ አካል ናቸው።

ህገ— ወጥነትን በመቆጣጠር እና አቅርቦትን በማሻሻል ገበያውን ለማረጋጋት እየተሰራ ያለው ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

ጥር 14/2017 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገበያ ማረጋጋት ፣ ገቢ መሰብሰብ ፣ ህገ –ወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ ሀይል ያለፉት ሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀን አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ በትኩረት በሚሰሩ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ባለፋት ሁለት ወር ከ አስራ አምስት ቀናት ንዑስ ኮሚቴው የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰትና ገበያውን ለማረጋጋት በሸማች ማህበራት በኩል እየተደረገ ያለ የመሠረታዊ ሸቀጥ አቅርቦት ስራ፣ በኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የፍጆታ ምርቶችን አቅርቦት ፣ የገቢ ስራን ከማሳደግ እና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ዕቅድ በየካ ክፍለ ከተማ ንግድ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ አለማየሁ ማሞ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች ዙሪያ የባዛር እና የሰንበት ገበያዎች ላይ የኢንዱስትሪ ፣የእንስሳት ተዋፅኦ እና የሰብል ምርቶች አቅርቦት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከእቅድ በላይ አቅርቦት ማቅረብ መቻሉ ተገልፃል፡፡

በመድረኩ የገቢ አሰባሰብ ስራዎች፣የተዘዋዋሪ ብድር አጠቃቀም እና አመላለስ በተመለከተ፣የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ስራዎች እና የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ፣በኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የተከናወኑ ተግባራትን ጨምሮ በግብረ ሀይሉ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የውይይት መድረኩን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ እንደገለፁት ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር እና አቅርቦትን በማሻሻል ገበያው ለማረጋጋት እየተሰራ ያለውን ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በመግለፅ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚደረጉ ድጎማዎችን ለማሳደግ የገቢ አሰባሰብ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ብርሀኑ ረታ አያይዘውም አያይዘውም በኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ላይ በልዩ ትኩረት በመስራት ነዋሪው ምርቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ግብረ ሃይሉ በቀጣይም የምርት አቅርቦት ተደራሽነቱን አጠናክሮ የማስቀጠል ስራ እንደሚሰራ እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በመስጠት የክትትል እና ድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል በመድረኩ ተገልፃል፡፡

አስተዳደሩ አካል ጉዳተኞች ተደራጅተው ከሚሰሩባቸው ድርጅቶች ጋር ባጋጠሟቸው ችግሮች ዙሪያ ውይይት አደረገ፡፡

ጥር 9/2017 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አካል ጉዳተኞች ተደራጅተው ከሚሰሩባቸው ከሀገር ጥበብ ማደራጃ እና ከአዲስ የቤትና የቢሮ እቃዎች ድርጅት ከስራ ሃላፊዎች እና ከቦርድ አባላት ጋር በስራቸው ባጋጠሟቸው የአሰራር ግድፈቶችና ችግሮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው አስራት ውይይት መድረኩን የመሩ ሲሆን አካል ጉዳተኞች ተሰማርተው በሚሰሩበት ተቋማት የአሰራር ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚገባ በመግለፅ አስተዳደሩም እግር በእግር ተከታትሎ ችግሮችን በመፍታት የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የድርጅቶቹ የስራ ሃላፊዎች በስራቸው እያጋጠሙ ስላሉ ጉዳዮች ለቦርድ አባላቱ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቦርድ አባላቱ ውሳኔ በሚያስፈልጉ አስራሮች ላይ ሃላፊነት ወስዶ መስራት እናዳለበት አስረድተዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ማህበራዊ ጉዳይ አማካሪና የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ተወካይ ወ/ሮ መሰረት መካሻ በበኩላቸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር እና ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ድርጅቶቹ ያሉባቸውን የአሰራር ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በድርጅቶቹ የስራ ሃላፊዎች የተነሱ የአሰራር ግድፈቶች እልባት በሚያገኙባቸው ጉዳዮች ላይ አቶ እንዳልካቸው አስራት የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎችና አስተዳደር ጽህፈት ቤት 368 አንቀሳቃሾችን ያቀፈ ለ112 ማህበራት የመስሪያ ቦታ ቁልፍ አስተላለፈ ጥር 9/2017ዓ.ም

የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የመስሪያ ቦታዎችና አስተዳደር ጽህፈት ቤት 368 አንቀሳቃሾችን ያቀፈ ለ112 ማህበራት የመስሪያ ቦታ ቁልፍ አስተላልፏል። በመርሀ ግብሩ የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት እንደገለፁት ወጣቶች የተሻለ ነገን ለማየት ዛሬ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል፣ ዛሬ የመስሪያ ቦታ የተሰጣችህ ወጣቶች በተደራጃችሁበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት ከእራሳችህ አልፎ ለሌሎች የስራ ዕድል ለመፍጠር በትጋት መስራት ይገባችሀል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመስሪያ ቦታዎችና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አበባው ለሚ በበኩላቸው ማህበራቱን ውጤታማና ምርታማ እንድሆኑ ሙያዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር አስተዳደሩ ከጎናቸው መሆንኑ በመግለፅ ማህበራቱ በሚቀጥሉት ቀናት ውል ተዋውለው ወደ ስራ የሚገቡ መሆኑን ገልፀዋል።

በንግድ ዘርፍ 134 አባላት ያሉት ያቀፈ 69 ማህበራት፣ ማኑፋክቸሪግ ዘርፍ 46 አባላት ያሉት 9 ማህበራት እና በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተቀመጡ የሸገር ዳቦ ኮንቴነር 188 አባላትት ያሉት 34 ማህበር አጠቃላይ 368 አንቀሳቃሾችን ያቀፈ 112 ማህበራት የመስሪያ ቦታ ቁልፍ ተረክበዋል።

የጥምቀት በዓል ፈፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራውን ማጠናቀቁን የየካ ክፍለ ከተማ የፀጥታ ጥምር ግብረ—ሀይል አስታወቀ ጥር

9/2017 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ የፀጥታ ጥምር ግብረ—ሀይል የጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እና በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የከተማ ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን እንደገለፁት የከተራና የጥምቀት በዓል በወንድማማችነት፣ በህትም አማችነት እና በአንድነት የሚከበር በመሆኑ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጥምቀት በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የማይፈልጉ ሀይሎችን ሴራቸውን በማክሸፍ ዘላቂ ሰላማችንን ማስቀጠል ይገባል፤ ይህ የሚሆነው ሁላችንም በቅንጅት መስራት ስንችል ነው ሲሉ አቶ በላይ ደጀን አክለዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው የከተራና የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሚወጣው ምዕመን ምንም የፀጥታ ስጋት ሳይገባው በደስታ አክብሮ እንዲመለስ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የፀጥታ አካላትን በማወያየት ቅድመ ዝግጅት ስራውን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን በመግለፅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን የፀረ ሰላም ሀይሎችን ሴራ ማክሸፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የከተራና የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ከማድረግ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት እንዲያከብር ከአጎራባች ከተሞችና ክፍለ ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አቶ ብርሃኑ ረታ አክለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ሀላፊ ኮምሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል በበኩላቸው በዓሉ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን በማንሳት በቀጣይ ቀናትም የፀጥታ ግብረ—ሀይሉ የጀመረውን ቁጥጥርና ክትትል ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል ስምሪት የተሰጠው የፀጥታ አካል ከህብ ተሰቡ ጋር በመቀናጀት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡም የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ህብረተሰቡ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር አክብሮ ወደ ቤቱ እንዲመለስ የሰላም ሰራዊቱን እና በየደረጃው ያሉን መዋቅሮችን ከፀጥታ አካላት ጋር አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አቶ መገርሳ ገላና አፅንኦት ሰጥተውበታል። በክፍለ ከተማው 31 ደብር የሚገኝ ሲሆን 12 የታቦት ማደሪያ ቦታዎች መኖራቸውን እና በሁሉም ቦታ ዝግጅት መጠናቀቁን በውይይቱ ተገልፆል። በግምገማ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ሀላፊ ኮምሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላናን ጨምሮ የከተማ ደጋፊ አመራሮች የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የፀጥታ ጥምር ግብረ ሀይል አባላት ተገኝተዋል።

የጥምቀት በዓል የህዝቦችን ትስስር በማጠናከር ፣ቱሪዝምን በማሳደግ እና ከተሞችን በማነቃቃት ረገድ ትልቅ ሚና አለው፡-አቶ ጃንጥራር አባይ

የጥምቀት በዓል የህዝቦችን ትስስር በማጠናከር ፣ቱሪዝምን በማሳደግ እና ከተሞችን በማነቃቃት ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

የጥምቀት በዓል በጃን ሜዳ በድምቀት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን በመወከል መልእክት ያስተላለፉት አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በየዓመቱ በድምቀት እንዲከበር ከሀይማኖት አባቶች ጋር እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የጥምቀት በዓል በተመድ የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ታላቅ በዓል መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በዓሉ በአዲስ አበባም ሆነ በመላው ሀገሪቱ ከዳር እስከ ዳር በታላቅ ድምቀት እየተከበረ እንዳለም አውስተዋል፡፡ አዲስ አበባ ህብረ ብሄራዊ ከተማ እንደመሆኗ የሀይማኖቶች ልዩነት እና ገደብ ሳይኖር ሁሉም በእኩል የሚስተናገዱባት ከተማ መሆኗም ገልጸዋል፡፡

በዓሉ በከተማዋ በሁሉም አድባራት ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ እንደሚገኝም አውስተዋል፡፡በዓሉ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ በዓል እንደመሆኑ ከተለያዩ ዓለማት የመጡ ቱሪስቶች እና ጎብኚዎች መታደማቸውንም አቶ ጃንጥራር ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያን እና የአዲስ አበባን ገጽታ ከፍ በማድረግ ረገድ ሁሉም ዜጋ የአምባሳደርነት ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው በዓሉ በድምቀት እንዲሁም ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ወጣቶች፣ የጸጥታ ሐይሎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የከተራ እና የጥምቀት በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት ተጠናቋል

በአዲስ አበባ በተካሄደው የከተራና የጥምቀት በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳያጋጥም ተከብሮ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽን መ/ቤቱ በዓሉ ያለአደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ ከሀይማኖት አባቶችና ከበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በመሆን ህብተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተገንዝቦ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

በዚህም በዓሉ ያለምንም አደጋ ክስተት ተከብሮ ማለፉን ነው ከኮሚሽን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው። ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግና የጥንቃቄ መልዕክቶች በማስተላለፍ ህብረተሰቡና የሚዲያ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል። በበዓላት ጊዜ የተደረጉ የጥንቃቄ ተግባሮች በመደበኛና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችም ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በባለ ጉዳይ ቀን የሚሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል

ታህሳስ 23/2017ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በተገኙበት እየተሰጠ ያለው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የነዋሪዎችን ጊዜ ጉልበትና አላስፈላጊ መጉላላት በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው ተገልጋዮች ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች የሴክተር ተቋማት አመራሮችም በቢሯቸው ተገኝተው ተገልጋዮችን በማስተናገድ ላይ መሆናቸውን ተዘዋውረን ለመመልከት ችለናል።

የባለጉዳይ ቀን የማህበረሰቡን ጥያቄ ከመመለስ አኳያ የላቀ ሚና እየተወጣ ይገኛል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ5ቱን የጳጉሜን ቀናት የንቅናቄ ስራ የቅድመ ዝግጅት አፈፃፀም ገመገመ

ነሀሴ 28/2016 የካ ኮሙኒኬሽንRead More

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እና የከተማ አመራሮች በዚህ ምሽት በየካ ሾላ መብራት መንገድ ዳርቻ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት ድምቀት የሚሰጡ ችግኝ በመትከል በድጋሚ አሻራቸውን አኑረዋል።Read More

“የተዘጋ በር መክፈቻ ቁልፍ እሳቤን መቀየርና ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ መሆን ነው”!!
አቶ ብርሃኑ ረታ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ
Read More

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለሰጡን እውቅና እጅግ አድርገን እናመሠግናለን!!Read More

የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ከአቶ ጃንጥራር አባይ ጋር ከቤልጄም ኤምባሲ መገናኛ ያለውን የመንገድ ኮሪደር ልማትን ተዘዋውረው ጎበኙRead More

አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በየካ ክፍለ ከተማ በ2ኛው ምዕራፍ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚተገበርባቸውን ቦታዎች ተዘዋውረው ጎበኙRead More

የየካ ክፍለ ከተማ ፕላን ልማት ጽ/ቤት ክፍለ ከተማውን በፕላን የሚመራ ለማድረግ እና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በርካታ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገለፀ

ነሀሴ 28/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የመስመር ማዛወር ስራ ተጠናቀቀ

ግንቦት 2 /2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More

የቲቢ በሽታን ለመከላከል ለሚሰራው የቲቢ ምርመራ ዘመቻ ስራ ለዘርፉ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More

አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ማራኪ ለማድረግ በአምስት አቅጣጫ የኮሪደር ልማት ስራው እየተፋጠነ ይገኛል።

በየካ ክፍለ ከተማም የኮሪደር ልማቱ ነዋሪውን በባለቤትነት በማሳተፍ እየተከናወነ ሲሆን በዛሬው እለትም በወረዳ 07 እና 08 የመንገድ ዳር የልኬት ስራውን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች ጋር በማጠናቀቅ ለትግበራው ዝግጁ የማድረግ ስራ ሰርቷል።

መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮን የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ የማሳደግ ንቅናቄ መርኃ-ግብር በወረዳዎችም ተጠናክሮ ቀጥሏል

መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More

በዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ የተመራ የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የመስክ ምልከታ አደረጉ ::

በሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ የተመራ በፊዴራል ደረጃ የተዋቀረው የሱፐር ቪዥን ቡድን የመስክ ምልከታ እያደረገ ይገኛል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቴክኖሎጅ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን፣ ከተማ ግብርና ፣ ስፖርት ማዘውተሪያዎችን ፣ደይኬር እና የክ/ከተማ ተቋማት ስራዎችንም ምልከታ እያደረገ ይገኛል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!!!

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽህፈት ቤት በ6 ወር የስራ አፈፃፀም በከተማ ደረጃ ተመዝኖ ከ11ዱ ክፍለ ከተማ 2ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነRead More

ባለጉዳይ ቀንን ምክንያት በማድረግ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጥር 15 /2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየውን የህይወት ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀRead More

አስተዳደሩ በከተራ፣ ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ በዓላት አከባበር ወቅት የተሰሩ የጸጥታ ሥራዎችን ገመገመ

ጥር 13/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማው የከተራ፣ ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ በዓላት አከባበር ወቅት የተሰሩ የጸጥታ ሥራዎችን ከከተማ ደጋፊዎች፣ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ የስራ አመራሮች ፣ከፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በጋራ ገምግሟል።Read More

የምስጋና መልዕክት!

የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓል በክፍለ ከተማችን በሁሉም የታቦታት ማደሪያዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ታቦታቱም በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።Read More

ለወረዳና ለክ/ከተማ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጠ

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በ3 የስልጠና አርስት ላይ ማለትም 1.webmail 2. acronis True lmage 3. A.A complaint management portal / የካ ክፍለ ከተማ የአይሲቲ ባለሙያዎች እና ለወረዳ የአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰቷል፡፡
ሕዳር 27/2016 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት

ዜና ሹመት

አቶ ብርሃኑ ረታ አበጋዝ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የአቶ ብርሃኑ ረታ አጠቃላይ የስራ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት እና ለሃገራቸው ያበረከቷቸውና እያበረከቱት ያለውን እንቅስቃሴ ለምክር ቤቱ አባላት በክፍለ ከተማው የመንግስት ተጠሪ ሃላፊ በአቶ መገርሳ ገላና ቀርቦ ሃሳብ ከተሰጠበት በኃላ በሙሉ ድምጽ ሹመቱ ፀድቋል።

አቶ ብርሃኑ ረታ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙRead More

ዜና ጉብኝት

የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በመንግስት ካፒታል እየተገነቡ ያሉ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጉኝተዋል።Read More

የክፍለ ከተማው ተቋማት በቅንጅታዊ ትብብር አሰራር ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

በየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት በተመራው የፊርማ ስነ ስርአት ተቋማት በቅንጅት እና በትብብር በጋራ በሚያሰራቸው ጉዳይ ላይ የትስስር ሪፖርት አቅርበው የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።Read More