Land Development and Management Office

Spread the love

አቶ መልካሙ ተገኝ

የካ/ክ/ከ/የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው  አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የተቋቋመበትን ተልዕኮ ለማሳካት እንዲያስችለው የባለፈው ዓመት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ እና የ10 እና 5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድን መሰረት በማድረግ የ2018 በጀት ዓመት መሪ እቅድ አዘጋጅቶ ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ሲያሳካ እንዲሁም በዘመናዊ የኮምፒውተር የመረጃ ስርአት በመታገዝ የተሳለጠ አገልግሎት ለተገልጋዩ ሲሰጥ ቆይቶ በአጠቃላይ በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ለመፈፀም የተጣሉ ግብና ተግባራትን በእቅዱ መሰረት በመመራት ፈፅሟል፡፡ እነዚህኑ ተግባራት ለማሳካት  በሦስቱ የድጋፍና ክትትል አግባቦች በመታገዝ እየፈተሸ ግብረ-መልሶችን በመስጠት፣ ቀጣይ የትኩረት አቅጣዎችን በማመላከትና አፈፃፀማቸውን በየወቅቱ ወቅታዊ አፈፃፀሞችንም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ሲያቀርብ ቆይቶ በበጀት አመቱ 6 ወራት  የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራትን ክንውን የሚገልፅ ይህንን ሪፖርት አዘጋጅቷል፡፡

  1. የተቋሙ ራዕይ፤ተልዕኮና እሴቶች
  1. የተቋሙ ራዕይ

በ2022 ዓ.ም ዘመናዊ የመሬት ልማትና አስተዳደር ስርዓት የተዘረጋበት፣ የላቀ አገልግሎት የሚሰጥበት እና የተገልጋይ እርካታ የተረጋገጠበት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡ 

  1.  የተቋሙ ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ ህጋዊ አሰራርን የተከተለ እና ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት ያማከለ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ስራ ማከናወን፣ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት፤የልማት ተነሺዎችን መልሶ በማቋቋም፣የመብት ፈጠራ ስራ፣ የመሬት ባንክና መረጃ አያያዝ የተቀናጀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስርዓትን በመዘርጋት የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ፍትኃዊ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፡፡

  1. የተቋሙ እሴቶች
  2. አሳታፊነት፣
  3. ግልፅነት
  4. ፍትሀዊነት
  5. የላቀ አገልግሎት መስጠት
  6. በኃላፊነት ስሜት መስራት
  7. ተጠያቂነት

1.3.  የሪፖርቱ ዓላማ

ይህ ሪፖርት በበጀት አመቱ የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ከእቅድ አንፃር የተተገበሩ ዋና ዋና  ተግባራትን አፈፃፀም ማሳየት ነው

1.4. የሪፖርቱ አስፈሊጊነት

  • ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ከእቅድ አንፃር የተተገበሩ ተግባራትን አፈፃፀም ማሳየት
  • የተጣሉ ግቦችና ተግባራትን ለማስፈፀም የተሰሩ የድጋፍ፣ክትትልና የግብረ-መልስ አሰጣጥ ስራንዎችን ማሳየት
  • የነበሩ ጥንካሬዎችንና እጥረቶችን እንዲሁም ከአፈፃፀም አንፃር ያጋጠሙ ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን ማሳየት
  • በተጨማሪም የተቀመጡ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚያሳይ መልኩ ለማሳየት

ክፍል ሁለት

  • የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ተግባር 1. የሲስተም አገልግሎቶችን  ማከናዎን

  • የሲስተም አገልግሎቶችን ለማከናዎን የዞካ ሲስተም ስንጠቀም መቆየታችን ይታወቃል ነገር ግን ከጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ጀምሮ ከዞካ ወደ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ  ተቀይሯል የአሁኑ የሲስተም አገልግሎት ከባለፈው(ከዞካ ሲስተም) አገልግሎት ጋር ሲነፃፀር ከፍጥነትና ከጥራት አንፃር የተሻለ ሲሆን ስራው የተጀመረው ቀደም ሲል በዞካ ሲስተም ላይ ያመለከቱትን ተገልጋዮች በጎግል ሽት ከ19/02/2018 ዓ.ም መመዝገብ በመጀመር ሲሆን ስራው የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች፡-
ተ.ቁየተከናወኑ ተግባራትመለኪያክንውን
1በማህደር ክፍል ሰራተኞች ለሰነድ አጣሪ አፕሎድ የተደረገ ማህደርቁጥር1633
2በሰነድ አጣሪ ፒክ የተደረገበቁጥር1393
3በጂ.አይ.ኤስ ባለሞያ ቤዝ ማፕ የተወራረሰበቁጥር538
4የቴክኒክ ባለሞያበቁጥር547
5በሊዝ ቡድን መሪ የፀደቀበቁጥር316
6በይዞታ ቡድን መሪ የፀደቀበቁጥር373
7ዲስፓቸር(የተሰራጨ የሲስተም ካርታ)በቁጥር285

ተግባር 2. የክርክር መዝገብ ውስጥ የገቡ 1742 ማህደራትን አስተካክሎ ምላሽ መስጠት

  • በ2018ዓ.ም በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራ ውስጥ 2025 ማህደራትን አስተካክሎ ምላሽ መስጠት ተችሏል አፈፃፀማችንም ከ 100% በላይ ነው፡፡

ተግባር 3. በ6 ወሩ 69,188,388 ብር ከመሬት ሊዝ አገልግሎቶች ገቢ መሰብሰብ

  • በ6 ወራት ውስጥ   ከዓመታዊ ሊዝ፣ ከውዝፍ፣  ከልዩ ልዩ ገቢ  የተሰበበ ብር 120,895,371.99( አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን  ስምንት መቶ  ዘጠና አምስት  ሺ  ሶስት  መቶ  ሰባ አንድ ብር  ከ99/100 ሳንቲም)  የተሰበሰበ ሲሆን አፈጻጸሙም   ከእቅድ  በላይ (174%)  ሲሆን  ይህን የከፈሉ ተገልጋዮች ብዛት ደግሞ  3,655 ናቸው ፡፡ለገቢ አሰባሰባችንም ከፍ ማለት ዋናው ምክንያት የገቢ ንቅናቄ እቅድ በማዘጋጀት ወደተግባር በመገባቱ እና በሞንታርቦ የቅስቀሳ ስራዎች መሰራታቸው እንድሁም ሁሉም ባለድርሻ ተጋግዞና ተረባርቦ በመስራቱ ነው፡፡

ተግባር 4. በ6 ወሩ ወደ መሬት ባንክ ከገቡ ቦታዎች ውስጥ 25 በመቶ (ለ222 ቦታዎች) ለሚሆኑት ኦዲት ማድረግ

  • ወደ መሬት ባንክ ከገቡ ቦታዎች ውስጥ 25 በመቶ (ለ222 ቦታዎችን)  ኦዲት ማድረግ ታቅዶ 396 ቦታዎችን ኦዲት ተደርገዉ ግኝቶች ተደራጅተዋል፡፡አፈፃፀማችንም 178% ነው፡፡
  • በኦዲት  ሥራዉ መሠረት የተገኙ ዉጤቶች
  • በአጠቃላይ በመጀመሪያዉ 6 ወር በተደረገዉ ኦዲት በአጠቃላይ በብርከ6.5ሚሊዮን የግለሰብና የመንግስት ብር ተመላሽ እንዲደረግ የተደረገ ሲሆን ከ150 ካሬ ሜትር በላይ የመንግስት መሬት ተመላሽ እንዲሆን ለሚመለከተዉ አካል አሳዉቀናል ፡፡

ተግባር 5.ለጨረታ የሚሆን የፀዳ መሬት ማዘጋጀት

  • ለ7ኛ እና 8ኛ ዙር ጨረታ የሚሆን በጥቅሉ 32 ፕሎት ወይም 19,533.22  ካ.ሜ መሬት በማዘጋጀት እና በመለየት ለቢሮ መላክ ተችሏል፡፡

ተግባር 6.የበጎ አድራጎት እና የኢንሸቲቭ ስራዎችን ማከናዎን

  • የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ቤት ማደስን በሚመለከት በ 2,500,000 ብር የሚገመት የአንድ አቅመ ደካማ ዜጋ ባለ ሶስት ክፍል ቤት እንደ አዲስ ገንብተን ቁሳቁስ አሟልተን አስረክበናል
  • የአረንጓዴ አሻራ ተግባራትን ማካሄድ/ 3440 ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ታቅዶ በ3 ዙር 3450 ችግኞችን መትከል ተችሏል
  • ወላጆቻቸውን ያጡ ወይም የገቢ አቅማቸው ደካማ የሆኑ ወላጆች ስር የሚተዳደሩ 5 ህፃናትን ለመደገፍ ታቅዶ በበጀት አመቱ የመጀመሪ 6 ወራት ውስጥ 45,350.28 ብር ከባለሙያዎች በፔይሮል ተሰብስቦ ድጋፍ ተደርጓል እንዲሁም የመአድ ማጋራት ተጠቃሚም ማድረግ ተችሏል
  • ማዕድ ማጋራት ስራን በሚመለከት እጅ ላጠራቸው ለማህበረሰብ አካላት እና ደመወዛቸው አነስተኛ ለሆኑ የተቋማችን ባለሙያዎች ማእድ ያጋራን ሲሆን ይህም በአይነት ሲገለፅ፡-
  • 5850 ኪ.ግ ዱቄት (690,935.29ብር)
  • 382 ሊትር ዘይት(150,500 ብር)
  • 3 በሬ (450,000 ብር)
  • ፓስታ 20 ፍሬ (2000 ብር )
  • እንቁላል 1000 (25000ብር)
  • 1 በግ(20000 ብር)

          በጠቅላላው ፡-1,338,435.29ብር ማዕድ ማጋራት ስራ ተሰርቷል

  • ባካሄድነው የደምልገሳ መርሀግብር 29 ስራተኞች ደም ለግሰዋል(29 ዩኒት ደም)