Events

Spread the love

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም፣ የካ ኮሙኒኬሽን

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ሃሳብ ለ18ኛ ጊዜ በየካ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በመርሀ ግብሩ የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ሰንደቅ ዓላማ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን አንስተው ላለፉት 18 ዓመታት ቀኑን ስናከብር በደምና አጥንት ተጠብቆ የቆየውን የሰንደቅ ዓላማችን ክብርና ሉዓላዊነታችንን ይበልጥ ለማፅናት እና ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ለማስገንዘብ ጭምር መሆኑን ገልፀዋል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ሉዓላዊነታችንን ለማፅናትና የሰንደቅ ዓላማችንን ክብር ከፍ ለማድረግ በሁሉም መስክ ሃገራዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት ዳግም ቃላችንን በማደስ መሆን አለበት ሲሉ አቶ እንዳልካቸው አስራት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጠጅቱ ደገፋ በበኩላቸው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ 8/63/2006 አንቀፅ 6 በሚደነግገው መሰረት በየአመቱ ጥቅምት በገባ የመጀመሪያው ሰኞ በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ አንስተው 18ኛው የሰንደቅ አዓማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ክብርን ከፍ በሚያደርግ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በመርሃ ግብሩ ሰንደቅ ዓላማ ርክብክብ ፣ቃለ መሃላ የመፈፀም እና ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በበዓሉ የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጠጅቱ ደገፋን ጨምሮ የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣የፊደራል ፖሊስ አባላት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና የአስተዳደሩ ሰራተኞች ተገኝተው በዓሉን አክበረዋል።

በሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ የኢሬፈና ስንስርዓት በመከናወን ላይ ነው:: Irreecha Hora Finfinneetti Sagantaan Irreeffannaa Gaggeeffamaa Jira.

“ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት! ” “Irreecha : Olka’iinsa Biyyaaf!”

ኢሬቻ 2018 “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት! ” በሚል መሪ ቃል ህብረብሔራዊ አብሮነትን በሚያጠናክሩ ዝግጅቶች በየካ ክፍለ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣ ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የየካ ክ/ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የ2018 ኢሬቻ ዋዜማ ህብር ብዝሀነትን በሚያንፀባርቁ ልዩ ልዩ ሁነቶች ተከብሯል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢሬቻ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው አቃፊው የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ ደምቀው የሚያደምቁት በዓል መሆኑን ገልፀዋል።

የማንሰራራት ዘመን ማሳያ የሆኑ ህዳሴ ግድብን የመሳሰሉ ፕሮጀክቶች በተጠናቀቁበት ፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶችም እንደሚጀመሩ በተበሰረበት በዚህ ዓመት የሚከበረው ኢሬቻ ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩና ድንቅ ነው ያሉት አቶ ሞገስ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሸጋገረው የገዳ ስርዓተ መገለጫ የሆነው ኢሬቻ እሴቶቹ ተጠብቀው በድምቀት እንዲከበር ከተማ አስተዳደሩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስገንዝበዋል

ኢትዮጵያ ህብረብሔራዊ ሀገር መሆኗን የምናሳይበት፣ የአዲስ አበባ ውበት ይበልጥ የሚጎላበት ኢሬቻ ፊንፊኔን ለማክበር ሁሉም በጉጉት እየጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሞገስ ለእንግዶች ተገቢውን ፍቅር በመለገስ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ የፍቅር እና የህብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነውና የኦሮሞ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ኢሬቻ ብሩህ ተስፋ አብሳሪ በዓል መሆኑን ጠቅሰው ለእንግዶች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት እሴትን በሚያጠናክር መልኩ ማክበር እንደሚገባ አስረድተዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና ኢሬቻ ፍቅርና አብሮነት የሚጠናከርበት ፣ በርካታ እሴቶች ያሉት የምስጋና በዓል መሆኑን ገልፀው እሴቶቹን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ማክበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት አባገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች እና የሀይማኖት አባቶች ለሀገራችን እና ለህዝባችን ማንሰራራትን ፣ ለመሪዎች ብርታትንና ፅናትን ፣ ለህዝባችን አብሮነትን በመመኘት ፀሎትና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ከየካ ክ/ከተማ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ቄሮዎች ፣ ቀሬዎች እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙ ሲሆን የኦሮሞን ቱባ ባህሎች የሚገልፁ እንዲሁም ብዝሀነትን የሚያሳዩ የብሔር ብሔረሰቦችንባህላዊ ውዝዋዜዎች በደማቅ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች አቅርበዋል።

መስከረም 20/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

የመስቀል ደመራና እሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲከበሩ በቅንጅት እንደሚሰሩ የአጎራባች ሸገር ሲቲ መነ አብቹ ከፍለ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

መስከረም 13/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከአጎራባች ሸገር ሲቲ መነ አቢቹ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር በመጪው ቀናት የሚከበሩትን የመስቀልና የእሬቻ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ህዝባዊ የውይይት መድረክ አካሄዷል።

በውይይቱ መድረኩ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ እንደገለፁት ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት የፍቅር፣ የአብሮነታችን ማሳያዎችና የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማጠንከሪያ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን በመሆናቸው በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ የአጎራባች የሸገር ሲቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች አበርክቷቸው የጎላ በመሆኑ በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለ ታደሰ በበኩላቸው እንደገለፁት የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ከአጎራባች ሸገር ሲቲ ከተማ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀይማኖታዊ የጨዋነት ማሳያን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።

የየካ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና ባቀረቡት የማወያያ ሰነድ ላይ እንደተናገሩት በዓላቶቹ ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የሸገር ሲቲ ነዋሪዎች ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በዓላቶቹ በሰላም ተከብረው እንዲውሉ የግንዛቤ ስራ በመስራት የአካባቢያችሁን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር የድርሻችሁን መወጣት ይገባል ብለዋል።

የሸገር ሲቲ መና አብቹ ወረዳ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ጉታ በበኩላቸው በአላቱ የጋራ ማንነት መገለጫዎች በመሆናቸው ሰላማቸው የተጠበቀ እንዲሆን የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ያሉ ሲሆን 2018 በጀት አመት ሰላም የሰፈነበትና የጋራ ሀገራዊ ውጤት የሚመዘገብበት እንዲሆን በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የሆኑ ከኦሮሚያ ሸገር ሲቲ ክፍለ ከተማ የመጡ ነዋሪዎች ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በዋነኝነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት በዓላቶቹ ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣለን ሲሉ ገልፀዋል ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁለቱም ክፍለ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደሲንቄዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የምስጋና መልዕክት


የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ የከተራና የጥምቀት በዓል በክፍለ ከተማው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ከፍተኛ አስዋፅኦ ለነበራቸው አካላት የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓል በክፍለ ከተማችን በሁሉም የታቦታት ማደሪያዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ 29 ታቦታቱም በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።

ታቦታቱ ወጥተው እስኪመለሱ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የክፍለ ከተማችን ፓሊስ መምሪያ አመራሮችና አባላት፣ የአድማ ብተና ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣ የሰላም ሰራዊት አባላት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በአጠቃላይ የፀጥታ አስከባሪ እና በየደረጃው የምትገኙ የከተማ ደጋፊ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሰላም ወዳዱ ህብረተሰባችንን በራሴና በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ ካለአንዳች የፀጥታ ችግር ሃይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ቀደም ሲል ጀምሮ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅራችን እና ባለድርሻ አካላት በመናበብ፣ በመደማመጥ፣ በመተሳሰብ፣ እና በመቀናጀት ስኬታማ ማድረግ በመቻሉም በቀጣይም ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ ላይ ሰርተን ውጤታማ የሆንባቸውን ተግባራት በመጭው የመሪዎች ስብሰባ ላይም መድገምና የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ በማስከበር የልማት ስራዎቻችንን ልናፋጥን ይገባል።

በመጨረሻም በዓሉ በደመቀና በአማረ መልኩ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የየራሳችሁን ድርሻ ለተወጣችሁ አካላት በሙሉ በድጋሚ ምስጋናዬ በየአላችሁበት ይድረስ።

አቶ ብርሃኑ ረታ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ

የየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ታቦት በህብረ ዝማሬና በሽብሸባ ታጅቦ ወደ መንበረ ክብሩ በሰላም ገብቷል።

ጥር 12/2017 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የጥምቀት በዓል በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በአማረና በደመቀ መልኩ ተከብሮ ታቦታቱ በዛሬው ዕለት በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ገብተዋል።

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላት የማጠቃለያ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከበር

ነሀሴ 25/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የክፍለ ከተማው ባህል ኪነ-ጥብና ቱሪዝም ፅ/ቤት በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል የሚከበረውን የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላትን ባህላዊ ቱፊቱን በጠበቀ ሁኔታ በድምቀት አክብሯል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ባህል ኪነ-ጥብና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አለሙ ኢምሮ የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላት መከበር ዓላማ የማህበረሰብን የአንድነት ግንባታ ማበልፀግና እሴቶቻችን ለቀጣይ ትውልድ በማሻገር የሀገርን ባህላዊ፣ ቱፊታዊ እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማስቀጠል፣ ማህበረሰቡ ትክክለኛ እሴቱን እንዲረዳ ለማድረግና በህዝቦች መካከል ወንድማማችና እህትማማችነትን ለማጠናከርና ለማጎልበት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓል አመጣጥ ባህላዊና እምነታዊ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ከቀደምት ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ የክረምቱን መውጣትና የበጋውን መምጣት አያይዞ የሚከበር ሲሆን ሴቶች በቡድን ሆነው ወገባቸው ላይ የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ ተክል አስረው አደባባይ ላይ በነፃነት እየሚጨፍሩ የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡

በዓሉም በክፍለ ከተማ ደረጃ በተለያዩ ኩነቶች የተከበረ ሲሆን በሴት ልጃ ገረዶች ልዩ ልዩ ውዝዋዜ እና የባህል አለባበስ ደምቆ ተከብሯል።