
አቶ ጎሳየ ሀሰን
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
መልዕክት
በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር
Yeka sub City Government
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት
Working premises development and Administration office
የዜጎች ስምምነት ቻርተር ሰነድ
/Draft Citizen Charter/

የነሀሴ 2017/ዓ/ም
አዲስ አበባ
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት
ኃላፊ መልዕክት
ማውጫ ገጽ
ክፍል አንድ.. 5
1.መግቢያ.. 5
1.1 የዜጎች የስምምነት ሰነድ ዓላማ… 5
1.2. የቻርተሩ አስፈላጊነት.. 5
1.3 የኤጀንሲው ሥልጣንና ተግባር.. 6
1.4 ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች.. 8
1.4.1 ራዕይ /Vision/ 8
1.4.2 ተልዕኮ /Mission/ 8
1.4.3 እሴቶች /Values/ 8
1.5 የጽ/ቤቱ ተገልጋዮች /ደንበኞች እና ባለ ድርሻ አካላት.. 9
1.5.1 የጽ/ቤቱ ተገልጋዩች.. 9
1.5.2 ጽ/ቤቱ ባለድርሻ አካላት.. 9
1.6 የጽ/ቤቱ የተገልጋዩ መብትና ግዴታዎች.. 10
1.6.1 የደንበኞች መብቶች.. 10
1.6.2 የደንበኞች ግዴታ… 10
1.6.3 የተቋሙ ግዴታ… 11
1.7 ለደንበኞች የምንገባው ቃል.. 11
ክፍል ሁለት.. 12
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት.. 12
2.1.1 የክፍለ ከተማ መዋቅራዊ አደረጃጀት.. 12
2.2 የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ዋና እና ዝርዝር አገልግሎቶች.. 13
2.2.1 ዋና ዋና አገልግሎቶች.. 13
2.2.2 ዋና ዋና እና ዝርዝር አገልግሎቶች.. 13
ክፍል ሶስት.. 14
3.1 ጽ/ቤቱ ዋናና ዝርዝር አገልግሎቶች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ.. 14
3.1.1 በክፍለ ከተማ በስታንዳርድ የሚሰጡ አገልግሎቶች.. 14
ክፍል አራት.. 17
4.1 የአስተያየትና የተሳትፎ ሁኔታ… 17
4.2 የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ስርዓት.. 17
አባሪዎች.. 19
1. የአገልግሎት መጠየቂያ ማመልከቻ ቅጻ ቅጽ.. 19
2. የዜጎች ቻርተር ትግበራ የተገልጋይ አስተያየት መቀበያ ቼክ-ሊስት.. 19
3. የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና በስሩ የሚገኙ የስራ ክፍሎች ስልክ ቁጥር 20
4. 20
1. አድራሻ.. 20
ክፍል አንድ
1.መግቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡
ስለሆነም ጽ/ቤቱ የሚሰጠው አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩን የመስሪያ ቦታ የማልማት አቅምና የተገልጋይ ፍላጎትን መሰረት የመስሪያ ቦታ አቅርቦት በፍትሀዊነት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የኤጀንሲው አመራሮችና ሠራተኞች ሊተገብሩትና ሊከተሉት የሚገባ ይህ የዜጎች ስምምነት ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡
1.1 የዜጎች የስምምነት ሰነድ ዓላማ
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ለኢንተርፕራይዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ከአድልዎ ነጻ በሆነ መልኩ በእኩልነትና በፍትሀዊነት ተደራሽ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ ነው።
1.2. የቻርተሩ አስፈላጊነት
ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ተገልጋዮች እንዲረዱ ለማድረግ፤
ተገልጋዮች ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተረድተው ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ እርካታቸውን ሊያሳድግ የሚችል አገልግሎት ለመስጠት፤
ባለድርሻ አካላትን እና ህብረተሰቡን በማሳተፍ ፍትህዊ አገልግሎት ለመስጠት፤
ጽ/ቤቱ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተገልጋዮች ባለቤት እንደሆኑ ተረድተው ተገቢና አቅምን ሊያሳድግ የሚችል አስተያየት፤ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፤
ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ (standard) ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፤
የዜጎችን የመረጃ ማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና
ጽ/ቤቱ ለዜጎች ግልፅ፤ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለበት አገልግሎት ለመሥጠት ያለመ መሆኑን ለማረጋገጥ፤
1.3 የኤጀንሲው ሥልጣንና ተግባር
ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች ማምረቻ፣ ማሳያ ፣ መሸጫ ሼድና ህንጻ መገንባት እንዲችል ከሚመለከተው አካል የለማ መሬት ይረከባል፤ እንዲሁም ካርታ የሌላቸው ነባር ይዞታዎችን እና አዲስ የሚሰጡ ቦታዎችን ካርታ እንዲሰራላቸው ያደርጋል፤
ለአዳዲስ የመስሪያ ቦታ ግንባታ አዳዲስ የዲዛይን ስራዎች እንዲከናወኑ ዲዛይን ከሚያዘጋጀው አካል ጋር በጋራ የዲዛይን ስራ እንዲሰራ ያደርጋል፤
ለኢንተርፕራይዝ እና ለአምራች ኢንዱስትሪ የሚውል የመስሪያ ቦታ ከሥራና ክህሎት ቢሮ እና ከኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ፍላጎት ይቀበላል፤ ይደለድላል፤ በከንቲባው ያፀድቃል፤
ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙባቸውን የማምረቻ ፣ ማሳያ ፣ መሸጫ ሼዶች ፣ ህንፃዎች በኢንዱስትሪ መንደሮች ፣ በክላስተር ማዕከላትና በገበያ ማዕከላት በማደራጀት ያስገነባል የመሰረተ ልማት አውታሮችም እንዲሟላላቸው ያደርጋል፤
ቀድመው የተገነቡትንም ሆነ አዲስ የሚገነቡ የመስሪያ ቦታ ማዕከላትን ስታንዳርድ ያወጣል፣ ሲፀድቅ ይተገብራል፣ ይቆጣጠራል፤
የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚዎች ለሆኑ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ፣ማሳያ እና መሸጫ ቦታ በውል ያስተላልፋል፤ የመጠቀሚያ ኪራይ በወቅቱ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡
በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ወይም የሚዘጋጁ የመስሪያ ቦታዎችን ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤
የመስሪያ ቦታ አሰጣጥ እና ማስተላለፍ የአሰራር ሥርዓት ጥናት ያቀርባል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
ዕድሳት እና ጥገና የሚያስፈልጋቸው መስሪያ ቦታዎችን በጥናት በመለየት የእድሳት እና የጥገና ስራ ያከናውናል፤
በህገ-ወጥ መንገድ የማምረቻ፣ ማሳያና መሸጫ ማዕከላት ተላልፈው ሲገኙ የተላለፈላቸውንም ሆነ የሚያስተላልፉ አካላት ላይ ክትትል ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
የመስሪያ ቦታዎች ሲተላለፉ ተጠቃሚዎች ከተዋዋሉበት የስራ ዘርፍ አላማና ተግባር ውጪ እንዳያውሉ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ አውለው ሲገኙም የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
በመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ይለያል፤ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል፤ ውጤቱንም ተግባር ላይ ያውላል፤
የክላስተር ማዕከላት ልማት ከኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እና ወቅታዊ መሆኑን በየጊዜው ያረጋግጣል፤ እንደአስፈላጊነቱ በመፈተሽ እንዲስተካከል የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ ተግባር ላይ ያውላል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
በመስሪያ ቦታ ውስጥ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች በመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ተግባራት ላይ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ያደራጃል፤
ለሚያደራጃቸው ኮሚቴዎች መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፤የአፈፃፀም ማኑዋል ያዘጋጃል፤ተግባርና ኃላፊነታቸውን በማሳወቅ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
በግል ፣ በመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ትስስር በመፍጠር ለኢንተርፕራይዞችና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታዎች እንዲገነቡ ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ተፈፃሚነቱን ያረጋግጣል፤
ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታዎችን ችግሮች በጥናት በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ለይቶ ያጠናል፣ ይቀምራል፣ ይተገብራል፣ ውጤታማነቱን ይከታተላል፤
ነባር የመስሪያ ቦታዎችን እና አዲስ የሚገነቡ መስሪያ ቦታዎችን በክላስተር ጽንሰ ሀሳብ መሰረት ያደራጃል፣ ተግባር ላይ ያውላል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
በመስሪያ ቦታ ማስተላለፍ እና አስተዳደር ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎችን ምላሽ እንዲጣቸው ያደርጋል፤
ክፍትና አዲስ የተገነቡ የመስሪያ ቦታዎችን መረጃ በየጊዜው በማጣራት ለከንቲባው ያሳውቃል፤
ለመካከለኛ እና ለከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በስታንዳርድ መሰረት ያስገነባል፣አስተዳደራዊ ሥራውን በተመለከተ የአሰራር ሥርዓት ያጠናል ወይም ያስጠናል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
1.4 ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
1.4.1 ራዕይ /Vision/
በ2022 ዓ.ም ዘመናዊ የመስሪያ ቦታ በማልማት አቅርቦቱን በማፋጠንና አስተዳደራዊ አሰራሩን በማዘመን በዘርፉ የተሰማሩ ኢንተርፕራዞች እና ኢንዱስትሪዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ማየት ፡፡
1.4.2 ተልዕኮ /Mission/
የዘርፉን እድገት ያማከለ ተጨባጭ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና መሰረተ ልማት የተሟላላት ደረጃውን የጠበቀ የመስሪያ ቦታ ገንብቶ በማስተላለፍ እና ፈጣን አገልግሎትን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ አስተዳደርን በመዘርጋት የኢንተርፕራዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡
1.4.3 እሴቶች /Values/
ግልጽነት
ተጠያቂነት
ፍትሀዊነት
ቁርጠኝነት
ውጤታማነት
አጋርነት
ስራ ፈጠራን ማበረታታት
ዘመናዊነት
1.5 የጽ/ቤቱ ተገልጋዮች /ደንበኞች እና ባለ ድርሻ አካላት
1.5.1 የጽ/ቤቱ ተገልጋዩች
1. መስሪያ ቦታ የሚጠይቁ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች
2. የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች
1.5.2 ጽ/ቤቱ ባለድርሻ አካላት
የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
የአዲስ አበባ ምክር ቤት
ፋይናንስ ጽ/ቤት
የኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፤
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት፤
የፍትህ ጽ/ቤት፤
የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት፤
የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት፤
የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት፤
የኢኖቬሽንና ቴክኖልጂ ልማት ጽ/ቤት
የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዲይ ጽ/ቤት፤
የገቢዎች ጽ/ቤት፤
የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት፤
የፕላንና ልማት ጽ/ቤት፤
የኢንቨስትመንት ጽ/ቤት፤
የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት፤
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት፤
የህብረተሰብ ተሳትፍና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፤
የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤
የምግብና መድሃኒት ጽ/ቤት፤
የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት፤
የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት
የውሃና ፍሳሽ ጽ/ቤት፤
የመሬት ይዞታ ምዛገባና መረጃ ኤጀንሲ፤
የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት፤
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፤
መንግስታዊ ያልሆኑ ጽ/ቤት
1.6 የጽ/ቤቱ የተገልጋዩ መብትና ግዴታዎች
1.6.1 የደንበኞች መብቶች
የጽ/ቤቱ የመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ደንብና መመሪያ የማወቅ መብት አላቸው ፤
በጋራ የመመካከር ሃሳባቸውን የማቅረብ መብት፤
ጽ/ቤቱ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶቹ ሙሉ መረጃ የማግኘት፤ የማወቅ እና የመጠቀም መብት፤
ተገቢው አገልግሎት ሳይሰጥ ሲቀር ቅሬታ የማቅረብና መፍትሔ የመጠየቅ መብት፣
ተጠቃሚ ኢንተርፕራዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት አላቸው።
በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ማንኛውንም ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ የማግኘት መብት አላቸው፤
ተገልጋዮች አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስቀድመው የማወቅ መብት አላቸው፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያየት /ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍትሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ የማግኘት፤
ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው፤
1.6.2 የደንበኞች ግዴታ
የጽ/ቤቱን ደንብና መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ፤
የጽ/ቤቱን ደንብና የአሰራር መመሪያ ተከትሎ መስራት፤
በማንኛውም ጊዜ ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ፤
የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታን መከተልና ማሟላት፤
የሚጠቀሙበትን የመሰሪያ ቦታ በአግባቡ መጠበቅ፤
ከጽ/ቤቱ ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር፤
1.6.3 የተቋሙ ግዴታ
የጽ/ቤቱን ደንብና መመሪያዎች ተገልጋዮች እንዲያውቁት ማድረግ፤
በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለመስጠት አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላት፤
ጽ/ቤቱ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሙሉ መረጃ ፣ የሙያ ድጋፍና ምክር መስጠት፤
በመስሪያ ቦታዎች አካባቢ የተገልጋዮችን ተሳትፎ ማጠናከር፤
በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት መስጠት፤
ለተገልጋዮች ፍትሃዊ ፣ከአድሎ የጸዳ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ አገልግሎት መስጠት፤
ተገልጋዮች የሚያቀርቡትን ቅሬታ መቀበል፤
ለተገልጋዮች ቅሬታ የሚሰጡ ምላሾችን በጽሁፍ መስጠት፤
ከተገልጋዮች ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር፤
1.7 ለደንበኞች የምንገባው ቃል
ጽ/ቤቱ በቻርተሩ ባስቀመጠው የአገልግሎት አሠጣጥ ስታንዳርድ መሠረት ሙሉ ለሙሉ ለዜጎች /ለተገልጋዮች/ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
የመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደርን በተመለከተ የመንግስትን ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ሕግ ፣ደንብ አሰራር እና መመሪያዎችን ተግባር ላይ እናውላለን፡፡
እሴቶቻችን ላይ ተመስርተን የኤጀንሲውን ተገልጋዮች በሙሉ በአክብሮት፣ በፍትሃዊነት እና ያለአድሎ እናገለግላለን፡፡
ብልሹ አሰራርንና የሙስና አመለካከትን በመታገልና ተግባሩንም በመጸየፍና በማስወገድ ከብልሹ አሰራርንና ከሙስና የጸዳ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
ክፍል ሁለት
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት
2.1.1 የክፍለ ከተማ መዋቅራዊ አደረጃጀት
2.2 የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ዋና እና ዝርዝር አገልግሎቶች
ጽ/ቤቱ 8 ዋና አገልግሎቶችና በስራቸውም 13 ዝርዝር አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን እነዚህም እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡
2.2.1 ዋና ዋና አገልግሎቶች
የመስሪያ ቦታ የማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት፣
የመረጃ አገልግሎት መስጠት፣
የመስሪያ ቦታ የኪራይ ውል አገልግሎት መስጠት፣
ቅሬታ መቀበልና መፍታት፤
የመስሪያ ቦታ ደህንነትን ማረጋገጥ፣
የመስሪያ ቦታ የዝውውር ማደረግ፤
የመስሪያ ቦታ መሰረተ ልማት ድጋፍ ማደረግ፤
የዕድሳት እና ጥገና አገልግሎት መስጠት፤
2.2.2 ዋና ዋና እና ዝርዝር አገልግሎቶች
የመስሪያ ቦታ የማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት፣
ለአዲስ ቦታ ተጠቃሚ ውል መስጠት፤
ለማስፋፊያ ቦታ ተጠቃሚ ውል መስጠት፣
የመረጃ አገልግሎት መስጠት፣
የመስሪያ ቦታ መረጃ ተደራሽ የማድረግ አገልግሎት መስጠት፣
የውል አገልግሎት መስጠት፣
የዉል ዕድሳት አገልግሎት መስጠት፣
ውል የማቋረጥ አገልግሎት መስጠት፣
ቅሬታ መቀበልና መፍታት፤
ቅሬታና አቤቱታዎችን መቀበል፣
ለቅሬታና አቤቱታ አቅራቢዎቹ ምላሽ መስጠት፤
የመስሪያ ቦታ ደህንነትን ማረጋገጥ፣
የማሽን ልኬት አገልግሎት መስጠት
የህንጻው የመሸከም አቅም ልኬት አገልግሎት መስጠት
የመስሪያ ቦታ የዝውውር ማደረግ፤
6.1 የዘርፍና የመስሪያ ቦታ ዝውውር አገልግሎት መስጠት
የመስሪያ ቦታ መሰረተ ልማት ድጋፍ ማደረግ፤
7.1. የውኃና የአሌክትሪክ መሰረተ ልማት እንዲሟላ ክትትል ማድረግ፤
የዕድሳት እና ጥገና አገልግሎት መስጠት፤
በበጀት በመደገፍ የጥገና እና የድሳት ማከናወን፣
በኢንተርፕራይዝ እና በአምራች ኢንዱስትሪዎች አቅም እድሳትና ጥገና ሲጠየቅ ፍቃድ መስጠት፣
ክፍል ሶስት
3.1 ጽ/ቤቱ ዋናና ዝርዝር አገልግሎቶች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ
3.1.1 በክፍለ ከተማ በስታንዳርድ የሚሰጡ አገልግሎቶች
3.1 ጽ/ቤቱ ዋናና ዝርዝር አገልግሎቶች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ
3.1.1 በክፍለ ከተማ በስታንዳርድ የሚሰጡ አገልግሎቶች
| ተ.ቁ | የሚሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶች | አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ | የአገልግሎት ስታንዳርድ/ደረጃ | አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታና ሁኔታ | አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጠየቅ ቅድመ ሁኔታ | |
| ጊዜ በሰዓት/ደቂቃ | ጥራት | |||||
| 1 | የመስሪያ ቦታ የማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት፣ | |||||
| 1.1 | ለአዲስ ቦታ ተጠቃሚ ውል መስጠት፤ | ክ/ከተማ | 30 ሰዓት | 100% | የውል ሰነድ በማዋዋል | የተሟላ የአደረጃጀት ሰነድ፣በፕሮሰስ ካውንስል የጸደቀበትና ቃለጉባኤና ደብዳቤ፣የንግድ ስራ እቅድ፣ |
| 1.2 | የማስፋፊያ ቦታ ለተጠቃሚ ውል መስጠት፣ | ክ/ከተማ | 30 ሰዓት | 100% | የውል ሰነድ በማዋዋል | የተሟላ የአደረጃጀት ሰነድ፣በፕሮሰስ ካውንስል የጸደቀበትና ቃለጉባኤና ደብዳቤ፣የንግድ ስራ እቅድ፣ ተጨማሪ የሰው ኃይል ቅጥር፣የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀትና ተጨማሪ ማሽን እንደሚያስፈልግ መረጃ ማቅረብ የሚችል |
| 2 | የመረጃ አገልግሎት መስጠት፣ | |||||
| 2.1 | መረጃ ተደራሽ የማድረግ አገልግሎት መስጠት፣ | ክ/ከተማ | 15 ደቂቃ | 100% | በቃልና በደብዳቤ | በአካል እና በማመልከቻ መጠየቅ |
| 3 | የውል አገልግሎት መስጠት፣ | |||||
| 3.1 | የዉል ዕድሳት መስጠት፣ | ክ/ከተማ | 30 ደቂቃ | 100% | የውል ሰነድ በማዋዋል | ነባር ውል፣የታደሰ ደረጃ እድገት፣ያለፈው በጀት አመቱ እስከ ጨረሻው ወር ክፍያ ደረሰኝ፣የገቢዎች ክሪላንስ፣ የግቢ ኮሚቴ ግዳታዎችን የተወጣበት ማረጋገጫ |
| 3.2 | ውል ማቋረጥ፣ | መስሪያ ቦታ የሚገኝበት ሳይት ላይ | 15 ደቂቃ | 100% | ቅድመ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በመስጠት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በመስጠት | የዘመኑ ውል እድሳት፣ የብድር ፣ ከመሳሪያ ሊዝና የውሃና መብራት እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ደብዳቤ |
| 4 | ቅሬታ መቀበልና መፍታት፤ | |||||
| 4.1 | ቅሬታና አቤቱታዎችን መቀበል፣ | ክ/ከተማ | 7 ደቂቃ | 100% | የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ በማስሞላት | በጽሁፍ የቀረበ የቅሬታ አቅራቢው ማመልከቻ |
| 4.2 | ለቅሬታና አቤቱታ አቅራቢዎች ምላሽ መስጠት፤ | ክ/ከተማ | 12 ሰዓት | 100% | የቅሬታ መመለሻ ቅጽ በመሙላት | በጽሁፍ የቀረበ የቅሬታ አቅራቢው ማመልከቻ |
| 5 | የመስሪያ ቦታ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ | |||||
| 5.1 | የማሽን ልኬት አገልግሎት መስጠት | ክ/ከተማ | 12 | 100% | የድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል ሳይት በመውረድ | የመስሪያ ቦታ ደህንነት አመላካች ጥናት፣ማመልከቻ ማቅረብ |
| 5.2 | የህንጻው የመሸከም አቅም ልኬት አገልግሎት መስጠት | ክ/ከተማ | 20 | 100% | የድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል ሳይት በመውረድ | የመስሪያ ቦታ ደህንነት አመላካች ጥናት፣ማመልከቻ ማቅረብ |
| 6 | የመስሪያ ቦታ የዝውውር ስራ ማመቻቸት፤ | መስሪያ ቦታ የሚገኝበት ሳይት ላይ | 3 ሰዓት | 100% | የድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል ሳይት በመውረድ | የመስሪያ ቦታ የዝውውር ፍላጎት ማመልከቻ የድጋፍ ደብዳቤና ተጨማሪ ደጋፊ ማስረጃዎች |
| 7 | የመስሪያ ቦታ መሰረተ ልማት ድጋፍ ማደረግ፤ | መስሪያ ቦታ የሚገኝበት ሳይት ላይ | 4 ሰዓት | 100% | የድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል ሳይት በመውረድ | የኢንተርፕራይዝ ወይም አምራች ኢንዱስትሪ ማመልከቻ ማቅረብ |
| 8 | የዕድሳት እና ጥገና አገልግሎት መስጠት፤ | |||||
| 8.1 | በበጀት በመደገፍ የጥገና እና የድሳት ማከናወን፣ | ክ/ከተማ | 24 ሰዓት | 100% | በጀት እንዲያዝ በማደረግ፣ ድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል ሳይት በመውረድ | የኢንተርፕራይዝ ወይም አምራች ኢንዱስትሪ ማመልከቻ ማቅረብ |
| 8.2 | በኢንተርፕራይዝ እና በአምራች ኢንዱስትሮዎች አቅም እድሳትና ጥገና ሲጠየቅ ፍቃድ መስጠት፣ | ክ/ ከተማ | 6 ሰዓት | 100% | የድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል ሳይት በመውረድ | የኢንተርፕራይዝ ወይም አምራች ኢንዱስትሪ ማመልከቻ ማቅረብ |
ክፍል አራት
4.1 የአስተያየትና የተሳትፎ ሁኔታ
ኤጀንሲው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ ዜጎች አስተያየት፣ ጥቆማ ፣ጥያቄ እና ማብራሪያ የሚሹ ከሆነ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች መሠረት በማቅረብ ለአገልግሎታችን መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጾዖ ማበርከት ይችላሉ፡፡
በአስተያየት መስጫ መዝገብ፤
በአካል በመገኘት፤
የአስተያየት መስጫ ፎርም በመጠቀም፤
በአስተያየት መስጫ ሳጥን በመጠቀም፤
በቢሮው መስመር ስልክ ስልከ ………………..
በቢሮው ፋክስ ————-
“ኢሜል” ———————-
ድህረ ገጽ www…………..
ቴሌግራም አካውንት—————
ፌስ ቡክ ገጽ——————-
በቢሮው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚቀርቡ አስተያየቶች ግብረ-መልስ የምንሰጥና በግልጽ የምናሳውቅ ሲሆን ለዚህም በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የመለጠፍ፣ “የኢሜል” ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገጽ አድራሻችንና ሌሎች መሰል መንገዶችን የመጠቀም አማራጮችን በመከተል ለተገልጋዩ እናሳውቃለን፡፡
4.2 የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ስርዓት
በቻርተሩ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት ያላገኘ ተገልጋይ ወይም ዜጋ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ሥርዓት በደንብ ቁጥር 78/2008 ሆኖ በሚከተለው አግባብ ይመራል፡፡
በአገልግሎታችን ቅሬታ ያደረበት/የገጠመው ተገልጋይ ወይም ዜጋ ቅሬታውን በቀጥታ አገልግሎቱን ለሰጠው ፈፃሚ በቃልና በጽሁፍ መግለጽ ይችላል፡፡
ቅሬታው የቀረበለት ፈፃሚም የቀረበለትን ቅሬታ አጣርቶ ወዲያውኑ ተገቢውን ምላሽ ለቅሬታ አቅራቢው መስጠት አለበት በተሰጠው መልስ ያልረካ ዜጋ ቀጥሎ ላለው ኃላፊ ቅሬታው እንዲፈታለት ማቅረብ ይችላል፡፡
የሥራ ኃላፊው ቅሬታውን አጣርቶ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡
የኃላፊው መልስ አጥጋቢ ካልሆነ ለኮምሽኑ ለሚመለከተው ዘርፍ ወይም ለቢሮው ጉዳዩን በተቀመጠው የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ በጽሁፍ በማቅረብ መፍትሄ ይጠይቃል፡፡
በመጨረሻም ተገልጋዩ ከስራ ክፍሉ ወይም ዘርፉ አጥጋቢ ምላሽ ካልሰጠው ከተቋሙ ውጪ ለሆነውና የህዝብ ቅሬታን ለሚቀበለው ክፍል/ለሚለከተው አካል ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
አባሪዎች
የአገልግሎት መጠየቂያ ማመልከቻ ቅጻ ቅጽ
አገልግሎት ሥራ ክፍል/ዳይሬክቶሬት፡—————————————————::
የአገልገሎት ጠያቂ ስምና አድራሻ፡———————————————————————————————————————————————————————————————————::
የሚፈለገው/ የሚጠየቀው አገልግሎት ዓይነት፡——————————————————————————————————————————————————————————————————-::
የዜጎች ቻርተር ትግበራ የተገልጋይ አስተያየት መቀበያ ቼክ-ሊስት
ተ.ቁ
የመገምገሚያ ነጥቦች
የግምገማ ነጥብ ደረጃ
4
3
2
1
1አገልግሎት ሰጭ ኃላፊ/ባለሙያየመስሪያ ቦታ አሰተዳደር፣ የደንበኞች አገልግሎትና ድጋፍ የተገልጋይ አቀባበል ሁኔታ
2ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት እንዴት ይመዝኑታል
3በቻርተሩ በተገለፀው መሰረት አግልግሎት ስለማግኘትዎ
4ፍትሀዊ አገልግሎት ስለማግኘትዎ
5ለቅሬታዎ ፈጣን ምላሽ ስለመሰጠቱ
እነዚህን እና የመሳሰሉትን ሌሎች የመገምገሚያ ነጥቦች ማካተት ይቻላል
የግምገማ ነጥብ አሰጣጥ መግለጫ
4 = እጅግ በጣም ጥሩ 3 = በጣም ጥሩ 2 = ጥሩ 1 = ዝቅተኛ
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት አመራሮችና በስሩ የሚገኙ የስራ ክፍሎች ስልክ ቁጥር
ተ.ቁ
ስም
የሥራ ክፍልና ኃላፊነት
ስልክ ቁጥር
የአጀንሲው አድራሻ
1
አቶ ጎሳዬ ሀሰን
የጽ/ቤት ኃላፊ
0923784527
መገናኛ የካ ክ/ከተማ ህንፃ
2
አቶ ጤናው አዘነ
የልማትና ማስተላለፍ አስተባባሪ
0912962219
>>
3
አቶ ብርሃነ ገ/መድህን
የመስሪያ ቦታ አሰተዳደር፣ የደንበኞች አገልግሎትና ድጋፍ ቡድን መሪ
0912463733
>>
4
አቶ ከበረ ስዩም
የመስሪያ ቦታ ማደራጀት፣ማስተላለፍና መረጃ ጥንቅር ቡድን መሪ
0910713029
>>
5
አቶ ዳዊት ማርቆስ
የመስሪያ ቦታዎች አካባቢ ምቹነትና እና ደህንነት ቁጥጥር ቡድን
0910123062
>>
6
ወ/ሪት ኤደን ዳንኤል
የመስሪያ ቦታ የልማት ስራዎች አቅርቦት ቡድን መሪ /ተወካይ
0913823195
>>
አድራሻ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት
አድራሻ፡- መገናኛ የካ /ክ/አስተዳደር ህንፃ
ስልክ ቁጥር +———–
ቴሌግራም https://t.me/workingpremises
ተገልጋዩ ህብረተሰብ የስልጣን እና የልማቱ ባለቤት ስለሆነ እኛ የህዝብ አገልጋዮች ህዝብን ማገልገል ታላቅ ክብር መሆኑን ተረድተን ተገልጋዩን ህብረተሰብ በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃል እንግባለን፡፡
አቶ ጎሳዬ ሀሰን
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

