የምስጋና መልዕክት
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ የከተራና የጥምቀት በዓል በክፍለ ከተማው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ከፍተኛ አስዋፅኦ ለነበራቸው አካላት የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓል በክፍለ ከተማችን በሁሉም የታቦታት ማደሪያዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ 29 ታቦታቱም በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።
ታቦታቱ ወጥተው እስኪመለሱ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የክፍለ ከተማችን ፓሊስ መምሪያ አመራሮችና አባላት፣ የአድማ ብተና ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣ የሰላም ሰራዊት አባላት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በአጠቃላይ የፀጥታ አስከባሪ እና በየደረጃው የምትገኙ የከተማ ደጋፊ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሰላም ወዳዱ ህብረተሰባችንን በራሴና በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በዓሉ ካለአንዳች የፀጥታ ችግር ሃይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ቀደም ሲል ጀምሮ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅራችን እና ባለድርሻ አካላት በመናበብ፣ በመደማመጥ፣ በመተሳሰብ፣ እና በመቀናጀት ስኬታማ ማድረግ በመቻሉም በቀጣይም ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ ላይ ሰርተን ውጤታማ የሆንባቸውን ተግባራት በመጭው የመሪዎች ስብሰባ ላይም መድገምና የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ በማስከበር የልማት ስራዎቻችንን ልናፋጥን ይገባል።
በመጨረሻም በዓሉ በደመቀና በአማረ መልኩ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የየራሳችሁን ድርሻ ለተወጣችሁ አካላት በሙሉ በድጋሚ ምስጋናዬ በየአላችሁበት ይድረስ።
አቶ ብርሃኑ ረታ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ

የየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ታቦት በህብረ ዝማሬና በሽብሸባ ታጅቦ ወደ መንበረ ክብሩ በሰላም ገብቷል።
ጥር 12/2017 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
የጥምቀት በዓል በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በአማረና በደመቀ መልኩ ተከብሮ ታቦታቱ በዛሬው ዕለት በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ገብተዋል።

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላት የማጠቃለያ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከበር
ነሀሴ 25/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
የክፍለ ከተማው ባህል ኪነ-ጥብና ቱሪዝም ፅ/ቤት በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል የሚከበረውን የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላትን ባህላዊ ቱፊቱን በጠበቀ ሁኔታ በድምቀት አክብሯል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ባህል ኪነ-ጥብና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አለሙ ኢምሮ የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላት መከበር ዓላማ የማህበረሰብን የአንድነት ግንባታ ማበልፀግና እሴቶቻችን ለቀጣይ ትውልድ በማሻገር የሀገርን ባህላዊ፣ ቱፊታዊ እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማስቀጠል፣ ማህበረሰቡ ትክክለኛ እሴቱን እንዲረዳ ለማድረግና በህዝቦች መካከል ወንድማማችና እህትማማችነትን ለማጠናከርና ለማጎልበት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓል አመጣጥ ባህላዊና እምነታዊ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ከቀደምት ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ የክረምቱን መውጣትና የበጋውን መምጣት አያይዞ የሚከበር ሲሆን ሴቶች በቡድን ሆነው ወገባቸው ላይ የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ ተክል አስረው አደባባይ ላይ በነፃነት እየሚጨፍሩ የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡
በዓሉም በክፍለ ከተማ ደረጃ በተለያዩ ኩነቶች የተከበረ ሲሆን በሴት ልጃ ገረዶች ልዩ ልዩ ውዝዋዜ እና የባህል አለባበስ ደምቆ ተከብሯል።









